
Ahadu Radio And Television
February 27, 2025 at 12:50 PM
*ዶ/ር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ*
የካቲት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዶ/ር አንዷለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን፤ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊቲ ሐኪም፣ ተመራማሪ፣ መምህር እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 1፡30 ሰዓት ገደማ ባልታወቁ ኃይሎች መገደላቸው ይታወሳል።
የፖሊስ መምሪያው የዶ/ር አንዷለም ዳኘ ግድያን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ የሟችን ግድያ በተመለከተ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን ገልጿል።
መግለጫውን የሰጡት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው፤ "የምርመራ ቡድኑ ከማኅበረሰቡ ጋር በመሆን በሠራው ሥራ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል" ብለዋል።
በዚህም በግድያ ወንጀሉ የተጠረጠረው ግለሰብ "እሱባለው ነበረ" የተባለ ግለሰብ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ወንጀል ፈጻሚው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ፍ/ቤት ቀርቦ ድርጊቱን መፈጸሙን ማመኑንም በመግለጫው ተመላክቷል።
ዋናው የወንጀሉ ፈጻሚ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የተናገሩት ኮማንደር ዋለልኝ፤ ተጨማሪ የወንጀሉ ተባባሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
