Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
February 28, 2025 at 02:16 PM
*897 አነስተኛ አምራች ድርጅቶች ወደ መካከለኛ አምራችነት ማደጋቸው ተገለጸ* የካቲት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት በተለያየ ችግር ሥራ ያቋረጡ 58 አምራቾች ወደቀደመ ሥራቸው ሲመለሱ 897 አነስተኛ አምራች ተቋማት ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ደረጃ ማደጋቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት አስታወቀ፡፡ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን ተወካይ ሥራ አስፈፃሚ ሮቤል አህመድ፤ ሥራ ያቋረጡት ተቋማት ስራ እንዲጀምሩ ከማድረግ ባሻገር በገበያው ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ራሳቸውን የሚያጠናክሩበት እገዛ ተደርጎላቸዋል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ የአምራች ድርጅቶቹ ዋነኛ ችግሮች የፋይናንስ አቅርቦት እና የመስሪያ ቦታ እጥረት እንደሆኑ ያስታወሱት አቶ ሮቤል፤ በቂ ነው ባይባልም ከፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር በመሆን የፋይናንስ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡ የማምረቻ ቦታዎችን በተመለከተም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራበት ይገኛል ብለዋል፡፡ "አምራቾች ጥራቱን የጠበቀ ተወዳዳሪ ምርት እንዲያርቱ የምናበረታታውን ያህል ሸማቹም የሀገር ውስጥ ምርቶችን በመግዛት አምራቾችን እንዲያበረታታ" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና ያለባቸውን ገንዘብ፣ የመሰረተ ልማት፣ የገበያና የክህሎት ችግሮችን ለመፍታት ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በህይወት ጌትነት #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *897 አነስተኛ አምራች ድርጅቶች ወደ መካከለኛ አምራችነት ማደጋቸው ተገለጸ*   የካቲት 21/2017 (አሐዱ ...

Comments