Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
February 28, 2025 at 04:43 PM
*በኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች ላይ የድርቅ ምልክቶች እየታዩ መሆኑ ተገለጸ* የካቲት 21/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች ላይ የዝናቡ ወቅት በመራዘሙ ምክንያት፤ የድርቅ ምልክቶች እየታዩ እንደሚገኝ የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ ለአሐዱ አስታውቋል። ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተ ድርቅ ሳቢያ በርካታ ሰዎች ተጎድተው እንስሳቱም በምግብ እጥረት የሞቱ ሲሆን፤ በተደረገው መጠነ ሰፊ ርብርብ ከጉዳቱ ማገገማቸው ይታወሳል። ሆኖም ግን አሁን ላይ ቦረናን ጨምሮ ጉጂ፣ ምስራቅ ሀረርጌና ሀረርጌ ዞኖች ላይ የድርቅ ምልክቶች እየታዩ እንደሚገኝ የክልሉ አደጋ መከላከል አስታውቋል። ምክንያቱም የዝናቡ ወቅት በመራዘሙ እጥረት በማጋጠሙ እንደሆነ የገለጹት የክልሉ አደጋ መከላከል ቡሳ ጎኖፋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኃላፊ ጥበቡ ኩምሳ፤ "በእነዚህ ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የድርቅ ምልክቶችና የውሃ እጥረት ያጋጠማቸውን ሪፖርቶች እየሰማን ነው" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል። በተለይም በቦረና አካባቢ አስፈሪ የድርቅ ምልክቶች እየታዩ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ጉዳት እንዳይደርስ ቀድሞ ለመከላከል ከመንግሥትና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል። በመሆኑም ምልክቶችን በማየት ቀደም ብሎ በተደረገ ጥንቃቄ አማካኝነት በአካባቢው የከፋ የውሃ እጥረት አለመኖሩንና የእንስሳት መኖም መኖሩን በማንሳት፤ እስካሁን ድረስ በሰውም ሆነ በእንስሳት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አስታውቀዋል። "ክልሉ በአሁኑ ሰዓት በ21 ዞኖችና 23 ከተማ መስተዳደሮች ላይ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ከተከሰቱ ደግሞ የመቆጣጠር ሥራዎችን በቅንጅት እየሰራ ይገኛል" ብለዋል። ስለሆነም የድርቅ ምልክት የታየባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰተ በመጣው የፈንታሌ ወረዳ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የደረሰውን አደጋ ለመቀነስና ወደ ከፋ ሁኔታ እንዳይደርስ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የጋራ እቅድ ወጥቶ እየተሰራበት እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በስፍራሽ ደመላሽ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *በኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች ላይ የድርቅ ምልክቶች እየታዩ መሆኑ ተገለጸ*   የካቲት 21/2017 (አሐዱ ሬዲ...

Comments