Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
March 1, 2025 at 08:47 AM
*ሕብረሰተቡ ጥራቱን የጠበቀ ምርት መግዛት ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለጸ* የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሕብረተሰቡ ሕጋዊነታቸው ካልተረጋገጠ ነጋዴዎችና የዋጋ ቅናሽ ካላቸው የተለያዩ ምርቶችን ከመግዛት ይልቅ፤ ጥራትን መሰረት አድርጎ መግዛት እንደሚገባው የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳስቧል፡፡ የባለስልጣኑ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወርቅነሽ ብርቄ፤ በተለያየ ወቅት በሕገ-ወጥ መንገድ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈበትና የተበላሹ እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ መድኃኒቶች፣ የመዋቢያና የምግብ ምርቶች መኖራቸውን ተናግረዋል። ስለሆነም ሕብረተሰቡ የሚያገኘው ምርት ዋጋው ስለቀነሰ ብቻ ቀጥታ ከመግዛት ይልቅ፤ ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባው አሳስበዋል። እንደ አዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የመጀመሪያው ተግባር የሕብረተሰቡን ጤና ማስጠበቅ መሆኑን የገለጹት የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ፤ ከዛ ወጥተው ሕገ-ወጥ ሥራን ሲሰሩ በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ ግን እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። ሆኖም ግን አንድ ተቋም ብቻውን ተቆጣጥሮ መከላከል ስለማይችል ሁሉም አካል በሕጋዊ መንገድ የተረጋገጡ ምርቶችን ብቻ በመጠቀም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይገባዋል ብለዋል። ሕገ-ወጥ አሰራሮች ሲኖሩም ተቋሙ በዘረጋው የጥቆማ መቀበያ መስመር አማካኝነት ጥቆማዎችን በመስጠት ተባባሪ መሆን እንደሚገባው በመግለጽ፤ በዚህ መንገድ ሕብረተሰቡን ተሳታፊ በማድረግ ሕገ-ወጥ ምርትንና አገልግሎትን ለመከላከል የሚያስችል የጤና ቁጥጥር ፎረም መመስረቱን አስታውቀዋል። የተመሰረተው ፎረም በሕገ-ወጥ ምግብና መድኃኒት ስርጭት ቁጥጥር ላይ መንግሥት ከሚያደርገው ክትትል በተጨማሪ፤ ሕብረተሰቡ የድርሻውን ኃላፊነት በመወጣት ሕገ ወጥ የመድኃኒትና የምግብ ስርጭት በጤና ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ አድርጎ መመስረቱን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከሕገ-ወጥ ምርት ጋር በተያያዘ በ2017 በጀት ዓመት 6 ወራት ውስጥ ግምታዊ ዋጋቸው ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችንና ከ32 ሺሕ ብር በላይ የሚያወጡ የተባላሹ ምግብና ጤና ነክ ምርቶች ማስወገዱን መግለጹ ይታወሳል። በስፍራሽ ደመላሽ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *ሕብረሰተቡ ጥራቱን የጠበቀ ምርት መግዛት ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለጸ*   የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲ...

Comments