Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
March 1, 2025 at 11:51 AM
*የሸገር ከተማ አስተዳደር ከገላን እስከ ዲማ የሚደርስ የባቡር መስመር ለመዘርጋት ማቀዱን አስታወቀ* የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሸገር ከተማ አስተዳደር ከገላን እስከ ዲማ የሚደርስ የባቡር መስመር ለመዘርጋት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ የተባለው የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በዛሬው ዕለት ባካሄደው ውይይት ላይ ነው። ሁለት ዓመት የሞላው እና 160 ሺሕ ካሬ ስፋት ላይ ያረፈው ሸገር ከተማ አምስት ከተሞችን በማዋሀድ የተፈጠረ ከተማ ነው። በከተማው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለጹት የሸገር ከተማ አሰሰተዳደር ከንቲባ ተሻለ አዱኛ (ዶ/ር)፤ ይህንን ተከትሎም ከሰሞኑ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ከንቲባው አክለውም፤ የዚህ ቀጣይ ውይይት በዛሬው ዕለት ከባንክ እና ፋይናንስ ተቋማት ጋር መደረጉን ገልጸዋል። ከንቲባው "ሸገር ከተማ የኢኮኖሚ ከተማ ነው" ያሉም ሲሆን፤ በቀጣይ በርካታ የልማት ሥራዎች እንደሚሰሩ አብራርተዋል። በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የባቡር መስመር የመዘርጋት ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ "ይህም ከገላን እስከ ዲማ የሚዘረጋ ይሆናል" ብለዋል። ከተማው የኮዬ ፈጬ አካባቢን ደግሞ የንግድ ቦታ የማድረግ ሀሳብ እንዳለው የገለጹ ሲሆን፤ በርካታ ሪልስቴት የሚሰራበት ቦታም ይሆናል ብለዋል። ሌላው የገላን ከተማን በከፍተኛ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ቦታ ለማድረግም ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል። በዛሬው ውሎም የፋይናንስ ተቋማት ሸገር ከተማ  በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል። በአቤል ደጀኔ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Comments