Addis Ababa Education Bureau
February 17, 2025 at 05:36 AM
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅግ ደማቅ እና ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ማምሻውን ተጠናቅቋል።
የህብረቱ ጉባኤ ለከተማችን ድምቀትና የኢኮኖሚ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የቱሪዝም መስህቦችን እና የከተማችንን መልካም ገጽታዎችን እንዲሁም የህዝባችንን ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
በዚህ በ38ኛው የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ እንደወትሮው ሁሉ እንግዳ ተቀባይነትና ያለባትን ተደራራቢ ሃላፊነት ስራው ከሚመለከታቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶች እና ከከተማችን ነዋሪዎችም ጋር በመሆን ላቅ ያለ የማስተናገድ ብቃትን ያሳየችበት ሲሆን ተባብረን በጋራ በሰራነዉ ስራ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ወንድሞች እና እህቶቻችን ኩራት መሆናችንን ዳግም አሳይተናል።
እንግዶቻችንም ባዩት ለዉጥ እየተደነቁ፣ በአዲስ አበባ መቆየት እየወደዱ እና ደግመው ደጋግመዉ መምጣትን እየተመኙ መሆኑን ሰምተናል።
የከተማችን ነዋሪዎችም ላሳያችሁት ታላቅ እንግዳ አክባሪነትና ተቀባይነት፣ እንዲሁም እንግዶችን ለማስተናገድ ዓላማ መንገዶች ሲዘጉ ፍጹም ትዕግስት እና ጨዋነታችሁ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ