Addis Ababa Education Bureau WhatsApp Channel

Addis Ababa Education Bureau

16.2K subscribers

About Addis Ababa Education Bureau

This channel intertain Educational activeties of Addis Ababa education bureau.

Similar Channels

Swipe to see more

Posts

Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
5/31/2025, 5:57:59 PM

https://www.tiktok.com/@aacaeb/video/7510668548226731269?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7497857878477588023

Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
5/31/2025, 8:54:43 AM

ለመምህራን ፣ርዕሳነ መምህራን እና ለሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት የጽሑፍ ምዘና ተሰጠ። (ግንቦት 23/2017 ዓ.ም) የጽሑፍ ምዘናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በ10 የምዘና ጣቢያዎች የተሰጠ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር አመራሮች በዳግማዊ ሚኒሊክ እና ኮከበ ጽበሀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው የምዘና ሂደቱን ተመልክተዋል። ምዘናው የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው የጽሑፍ ምዘና ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን እና ከመምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በየደረጃው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ከመስራቱ ባሻገር መዛኞችን እና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ ምዘናውን የሚያስፈጽሙ ባለሙያዎችን በየምዘና ጣቢያዎች መመደቡን እና ለጽሑፍ ምዘናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን የማሟላት ስራ መስራቱን አመላክተዋል። የሙያ ብቃት የጽሑፍ ምዘናው መምህራኑ በተመረቁበት የትምህርት አይነት እና የሚያስተምሩበትን የክፍል ደረጃ መሰረት አድርጎ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን በዛሬው ምዘና ከ9,700 በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች በከተማ አስተዳደሩ በተዘጋጁ 10 የምዘና ጣቢያዎች የጽሑፍ ምዘናው መሰጠቱ ተገልጿል። የጽሑፍ ምዘናው በአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተሰጠ ሲሆን ለጽሑፍ ምዘናው የተቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ የሚያመጡት ተመዛኞች በቀጣይ የማህደረ ተግባር ምዘና እንደሚሰጣቸው ከትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያሳያል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
❤️ 1
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/2/2025, 7:23:34 AM

የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (ግንቦት 25/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል" አገልጋይ መሪነት " በሚል ርዕስ የአገልጋይ መሪ ምንነትና ባህሪያትን መሰረት ያደረገ ሰነድ አቅርበዋል :: በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ትክክለኛ የአገልግሎት ስልቶችን በመረዳት እንደቢሮው ባህሪ የትምህርት ጉዳይን ጠንቅቆ በማወቅ ስራን የማስፈፀም አቅምን ማሳደግ እንዲሁም ባገኙት እውቀት መነሻነት ለመምራትና ለማገልገል ቁርጠኛ የሆነ ማንነት ከሁሉም አመራር ፣ ፈጻሚ ፣ ቡድን መሪና ዳይሬክተሮች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል :: የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለማግኘት https://linktr.ee/aacaebc

Post image
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/1/2025, 5:58:40 AM

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ወረገኑ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመማር ማስተማር ስራዉ ምቹ እንዲሆን ለማድረግ ተችላል፡፡ (ግንቦት 24/2017 ዓ.ም) በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 የሚገኘው ወረገኑ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉለት በማድረግ ለመማር ማስተማር ስራዉ ምቹ እንዲሆን ተደርጋል፡፡ ማህበረሰቡ ሲያነሳው የነበረዉን የረዥም ጊዜ ጥያቄ መሰረት በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት በመስራቱ በትምህርት ቤቱ አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች የጂ+4 ህንፃ ፣ የአስተዳደር ህንፃ እና የመጸዳጃ ቤቶች ተገንብተው እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ለረዥም ጊዜ ችግር ሆኖ የቆየውን የውሃ እጥረት ለመፍታት የከርሰ ምድር ውሃ የማጎልበት ሥራ በመስራት ለአገልግሎት እንዲዉል ተደርጋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
👍 1
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/2/2025, 10:07:22 AM

የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ:: (ግንቦት 25/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከምገባ አጄንሲ ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልእክት በ2018 ዓ.ም 1.2 ሚሊየን ለሚሆኑ ተማሪዎች ደንብ ልብስ ለመስጠት በከተማ አስተዳደሩ እቅድ መያዙን ገልፀው ስልጠናው በ2017 ዓ.ም የታዩ እጥረቶችን ለማረም በጥንካሬ የታዩትን አጠናክሮ ለመቀጠልና ተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል:: አቶ ሳምሶን አክለውም የደንብ ልብሱ በአግባቡ ካልተሰራ ተማሪዎች የደንብ ልብስ እንዲያጡ ብሎም የመንግስት ሀብት እንዲባክን የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት የስልጠናው ተሳታፊዎች ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ አቅርቦት እንዲኖር በኃላፊነትና በባለቤትነት ስሜት የጥራት ቁጥጥሩን እንዲያደርጉ አሳስበዋል:: የምገባ ኤጀንሲ ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር አቶ ቢንያም በበኩላቸው በስልጠናው የተነሱ ሃሳቦችን በመውሰድ የተሻለ ጥራት ያለው የደንብ ልብስ ለማሰራጨት ኤጀንሲው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀው የጥራት ኮሚቴው የጥራት ችግር እንዳያጋጥም ልብሱን ሲረከቡ ጥራቱን በትኩረት በማረጋገጥ እንዲሆን አሳስበዋል:: በስልጠናው ላይ የደንብ ልብስ ጥራት ለማረጋገጥ የሚረዱ ነጥቦች የያዘ ሰነድ የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ አቶ ዳግም አለማየሁ እና የጎፋ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ቴክስታይል አሰልጣኝ አቶ ኃይልዬ ዘውዱ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤት መሻሻል ምክትል ርዕሳነ መምህራን: የክፍለከተማና ወረዳ ተ. ወ. ማ ተወካዮች እና የተማሪ ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር ኮሚቴ ተወካዮች ተሳትፈዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
👍 1
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/1/2025, 2:06:07 PM

የሀዘን መግለጫ (ግንቦት 24/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርንና የኢትዮጵያ የተማሪ ወላጅ ማህበርን ለረጅም አመታት እስከ መጋቢት 2016 ዓ.ም ድረስ ሲመሩና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ኢንጂነር ጌታቸው ሠጠኝ ከዚህ አለም ድካም በማረፋቸዉ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ቢሮ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ጋደኞቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/3/2025, 2:45:08 PM

“ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ሃሳብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ (ግንቦት 26/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ሃሳብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች በተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ ላይ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት ተካሄዳል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልእክት መንግስት የሲቪል ሰርቫንቱን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ለህብረተሰቡ ለማድረስ በርካታ ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ውይይቱ በሲቪል ሰርቫንቱ መካከል ሀገራዊ አንድነት ለማጠናከርና በሀገራችን እድገት ላይ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት በማቀራረብ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የራሱ በጎ ተፅዕኖ እንደሚኖረው አስረድተዋል :: ሀላፊው አክለዉም የውይይቱ ተሳታፊዎች በሀገራዊ መግባባት ላይ የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ሚና እንዳለው በማሰብ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ በነፃነትና በንቃት መሳተፋቸዉን ገልጸዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር መድረኩ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎቱ በለውጡ ሥራ ምን ተግባር ነበረው የሚለው ሀሳብ ላይ ግልፀኝነት እንደሚፈጥር አብራርተው በሀገራዊ ጉዳይ ላይም በቂ መረጃ እንዲኖረው ያደርጋል ብለዋል :: የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ሰነዱ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሰራተኞች በቂ መረጃ እንዲኖራቸዉ ከማድረግም ባሻገር ብቃት ያለው ሰራተኛ ለሀገር ብልፅግና መረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ሰራተኞች ተረድተው ለዚህ መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል። በመጨረሻም በቀጣይ በከተማ አስተዳደሩና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄድ ውይይቶች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች ምርጫ ተካሂዷል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/3/2025, 10:05:53 AM

የአፍሪካ ቀዳማዊ ልጅነት ልማት ማዕከል በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ግብረመልስ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተካሄደ። (ግንቦት 26/2017 ዓ.ም) ዳሰሳዊ ጥናቱ በ26 የመንግስት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ተግባራዊ የተደረገው ጫወታን መሰረት ያደረገው የማስተማር ስነ ዘዴ በህጻናቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ያበረከተው አስተዋጽኦ ምን እንደሚመስል እና ወደ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ለመሸጋገር ምን ያህል ዝግጁ እንደሆኑ ለማረጋገጥ መካሄዱን በውይይቱ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የቀዳማዊ ልጅነት ፕሮግራም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ተግባራዊ ሆኖ ህጻናቱ ጫወታን መሰረት ባደረገው የማስተማሪያ ስነዘዴ አማካይነት ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ የግብአት አቅርቦትን እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ጨምሮ በሚያደርጋቸው የተለያዩ ድጋፍና ክትትሎች ተቋማቱ ትራንስፎርም በመሆን ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው የአፍሪካ ቀዳማዊ ልጅነት ልማት ማዕከል በዘርፉ የከናወኑ ተግባራት ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ በጥናት በማረጋገጥ ምክረ ሀሳብ በማቅረቡ ምስጋና ለማዕከሉ አቅርበዋል። የአፍሪካ ቀዳማዊ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ከበደ ወርቁ በበኩላቸው ማዕከሉ ትኩረት አድርጎ ከሚንቀሳቀስባቸው ዘርፎች አንዱ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን መስራት እንደመሆኑ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ በመተግበር ላይ ያለው ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ በህጻናቱ ሁለንተናዊ ዕድገትም ሆነ ወደ 1ኛ ደረጃ ለመሸጋገር ምን ያህል ብቁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ዳሰሳዊ ጥናት መደረጉን ገልጸው ማዕከሉ በጥናቱ የቀረቡ ምክረ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአቅም ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀረበው የዳሰሳዊ ጥናቱ ምክረ ሀሳቦችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው በትምህርት ቢሮ እና በማዕከሉ አመራሮች ምላሽ ተሰቷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
6/3/2025, 5:57:02 AM

ከተማ አቀፉን የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመደገፍና ተገቢውን ክትትል ለማድረግ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ውይይት አካሄደ። (ግንቦት 26/2017 ዓ.ም) የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን፣ የመምህራን ማህበር አመራሮችን ጨምሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች የተውጣጡ አመራሮች የተካተቱበት አደረጃጀት ሲሆን በውይይቱ የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ከዚህ በፊት በከተማ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ዘንድሮ የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተያዘለት መርሀግብር መሰረት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚቋቋሙ የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቶች ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት የተለመደ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መውጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቱ የፈተና ማስፈጸሚያ እቅድ በማውጣት በየደረጃው የንቅናቄ መድረኮች መዘጋጀታቸውን የማረጋገጥ ፣የፈተና ስርጭትና ርክክቡ በጥብቅ ዲሲፒሊን መመራቱን ፣ፈተናው ወደ ፈተና ጣቢያዎች ሲሰራጭ በጉዞ ሂደትም ሆነ በሚቆዩባቸው ቦታዎች ደህንነታቸው መጠበቁን የማረጋገጥ እንዲሁም የፈተና አስፈጻሚዎች በመመሪያው መሰረት በጥንቃቄ እንዲመለመሉ ድጋፍ የማድረግን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ኃላፊነቶች የሚጠበቅበት መሆኑን አመላክተዋል። ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ194 የፈተና ጣቢያዎች ለ71,972 ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 4 የሚሰጥ ሲሆን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናው ደግሞ በ192 የፈተና ጣቢያዎች ለ 80,323 ተማሪዎች ሰኔ 10፣11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በውይይቱ ተገልጿል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

Post image
Image
Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
5/30/2025, 1:57:23 PM

https://youtu.be/cQr0lp1r62s

Link copied to clipboard!