Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 17, 2025 at 06:37 AM
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (የካቲት 10/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰርዓተ ትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌታሁን ጌታቸዉ በአካባቢ ብክለትና በመከላከያ መንገዶቹ ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ በማቅረብ እውቀታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ሰነዱ መቅረቡ የአካባቢ ብክለት በተለያዩ መንገዶች ሊከሰት እንደሚችል ሰራተኞች በቂ ግንዛቤ በመጨበጥና የመከላከያ መንገዶቹን በመረዳት ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት እረገድ የድርሻቸዉን መወጣት እንዲችሉ ያግዛል ብለዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments