Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 17, 2025 at 09:29 AM
የአጠቃላይ ሰራተኞች መረጃን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመሰነድ በሚያስችል ሶፍትዌር ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ (የካቲት 10/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመንግስት ሰራተኞችን አጠቃላይ መረጃ ወረቀት አልባ በሆነ የአቀማመጥ ስርዓት ለማደራጀት የሚያስችል (ICSMIS) ሶፍትዌር ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡ የሰራተኞችን መረጃ በወረቀት አልባ ስርዓት በማደራጀት በቀላሉ ስራዎችን በቅልጥፍና ማከናወን እንደሚያስችል የገለጹት የቢሮው የሰው ሃይል አስተዳደር ባለሙያ አቶ ደረጀ ደምሴ የአሰልጣኞች ስልጠናውን የሚወስዱ ባለሙያዎች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል በጥንቃቄና ትኩረት በመስጠት መረጃዎችን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ስራውን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ሰራተኞች በእጃቸው ያለውን የትምህርት መረጃዎች እንዲሁም የአጫጭር ስልጠናና እውቅና ሰርተፍኬቶችን ጨምሮ በመረጃነት እንዲያዝላቸው የሚፈልጉትን ሰነድ በተቀመጠው ጊዜ ለሚመለከተው አካል በመስጠት ለስራው መቃናት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡ በስልጠናው የተመረጡ የቢሮው ሰራተኞችን ጨምሮ የመነን ፤ የገላንና ብርሃን አይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ፤ የጽንሰሃሳብና የተግባር ላይ ስልጠናው የቢሮው ሲስተም አድምንስትሬተር በሆኑት አቶ እንዳሻው ተሾመ ለ3 ቀናት እንደሚሰጥ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments