Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 18, 2025 at 08:53 AM
የትምህርት ተቋማት የ2017ዓ.ም የግማሽ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ምዘና መካሄድ ጀመረ። (የካቲት 11/2017 ዓ.ም) ምዘናው የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችን ጨምሮ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ2017ዓ.ም የግማሽ አመት የቁልፍ ውጤት አመላካች ተግባራት እና የሪፎርምና አገልግሎት አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው የምዘናው የመጀመሪያ ቀን የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመዝነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ምዘናው የትምህርት ተቋማቱ በየማሽ አመት የቁልፍ ውጤት አመላካች ተግባራት አፈጻጸም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመገምገም በቀጣይ ተቋማቱን በግብረ መልሱ መሰረት በመደገፍ ወደ ተቀራራቢ አፈጻጸም ለማምጣት ታስቦ እንደሚካሄድ የምዘናውን ሂደት ለመመልከት በተወሰኑ ተቋማት በተገኙበት ወቅት ገልጸዋል። የቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፈንታሁን እያዩ በበኩላቸው ቢሮው ቀደም ሲል በሁለት ዙር ድጋፍና ክትትል በማድረግ በግብረ መልሱ ዙሪያ ከተቋማቱ አመራሮች ጋር ውይይት ማካሄዱን ጠቁመው የግማሽ አመት ምዘናው ተቋማቱ የድጋፍና ክትትሉን ግብረ መልስ መነሻ በማድረግ ምንያህል ውጤታማ መሆን ቻሉ የሚለውን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። ምዘናው ከተካሄደባቸው ተቋማት መካከል የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ደበሌ ፣የወረዳ 9 ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ለማ እንዲሁም የኮከበ ጽበሀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ደለለኝ አስማረ ምዘናው ተቋማቸው በቁልፍ ውጤት አመላካች ተግባራት እና አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል ያእያከናወነ የሚገኘውን ተግባር መሰረት አድርጎ በመካሄዱ በቀጣይ የምዘናውን ግብረመልስ መሰረት በማድረግ የተሻለ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments