Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 18, 2025 at 10:47 AM
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን! (የካቲት 11/2017 ዓ.ም) ዛሬ በበጎነት የመኖሪያ መንደር ለአቅመ ደካሞች እና የልማት ተነሺዎች ያስገነባናቸውን 192 የመኖሪያ ቤቶችን የያዙ ሁለት ባለ 9 ወለል ህንጻዎች ለነዋሪዎቻችን አስተላልፈናል:: በሰዉ ተኮር ስራዎቻችን ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ እየሰራን ባለነዉ ስራ በበጎነት የመኖሪያ መንደር ለመኖር ምቹ የሆኑ ሰባት ህንጻዎችን ገንብተን ለኑሮ ምቹ ካልሆኑ አካባቢዎች ለተነሱ የከተማችን ነዋሪዎች ያስተላለፍን ሲሆን፣ በበጎነት የመኖሪያ መንደር የመኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን የህጻናት መጫወቻ፣ የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ፣ የጸጉር እና የልብስ ስፌት የስራ እድሎች የተካተቱበት ፣ የዜግነት ክብርን የሚመጥን ፣ንፁህ እና ዉብ አካባቢን ለነዋርዎቻችን አስረክበናል:: ከተማችን እንደ ስሟ ውብ፣ አበባ እየሆነች ያለችዉ የነዋሪዎቿን ኑሮና አኗኗር በማሻሻል ጭምር ሲሆን የዘጐችን ሁለተናዊ ህይወት የመቀየር ስራ በመንግስ በጀት ብቻ እንደማይሳካ ገብቶን “መስጠት አያጎድልም “በማለት በርካታ ልበ ቀና ባለሀብቶችን በማስተባበር በመስራት የበርካቶችን ህይወት መቀየር ችለናል:: ዛሬ ያስተላለፍነዉን “ ከጎናችን በመቆም ድጋፍ ያደረገልንን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን አመራሮቹ እና ሰራተኞቹን በነዋሪዎቻችን እና በራሴ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments