Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 19, 2025 at 11:16 AM
ፍትሃዊ የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ፡- (የካቲት 12/2017 ዓ.ም) • የተማሪ ቅበላን 1,253,737(106%) ማድረስ ተችሏል፤ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር አፈፃፀሙ ሲነፃፀር 89,049 ብልጫ ያለዉ ነዉ፡፡ • የትምህርት ፍትሀዊነትን ከማስፈንም አካያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎች ቁጥር 33,672(100%) ማድረስ ተችሏል። • በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በተሰራዉ ስራ በገንዘብ 3,841,682,948.15፣ በዓይነት 137,566,563.36፣ በጉልበት 19,800,640.85 እና በእውቀት 26,380,054.45 በድምሩ ብር 4,025,430,206.81 በመሰብሰብ የትምህርት ግብዓትን ማሟላት ተችሏል፡፡ • በዘላቂነት የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ግብዓትን ከማቅረብ አንፃርም ለ1,037,500 (100%) ተማሪዎች ዩኒፎርም፤ለ9,125,435 (100%) ተማሮዎች ደብተር በማሰራጨት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። • በተማሪ ምገባ አገልግሎት 835,069 (100%) ተማሪዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ የተቻለ ሲሆን የተማሪ የቅበላ አቅም ለማሻሻልና የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋጋጥ የተሰራው ስራ አበረታች ዉጤት አምጥቷል፡፡ • በከተማችን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ተገቢነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ በ126 ተቋማት ላይ የውጭ ኢንስፔክሽን በማካሄድ የደረጃ ምደባ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች ተደራሽ ተደርጓል። • ለትምህርትና ስልጠና የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ጥያቄ ላቀረቡ 660 (94.7%) ተቋማት የእውቅና እና የእድሳት ተሰጥቷል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments