
Addis Ababa Education Bureau
February 22, 2025 at 10:16 AM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የተግባር ሥራ (CTE) ለሚያስተምሩ መምህራን ስልጠና በመስጠት መሆኑን ገለፀ::
(የካቲት 15/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በ 11ዱም ክፍለ ከተማዎች ለሚገኙ የተግባር ሥራ (CTE) መምህራን የ 3 ቀናት ስልጠና መስጠት ጀምሯል::
ስልጠናው በዋናነት የተግባር ትምህርት (CTE) የሚያስተምሩ መምህራን የመማር ማስተማር ስራውን በሚፈለገው መንገድ ማስተማር እንዲችሉ ግንዛቤ የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አሊ ከማል ሰልጠናውን ተዘዋውረው በተመለከበት ወቅት ሰልጣኝ መምህራን ክፍለዘመኑ የሚፈለገውን እውቀት በመያዝ ከንድፈ ሀሳብ በዘለለ በተግባር ላይ ትምህርት ብቁና ሥራ ፈጣሪና እንዲሁም ራሱን መግለፅ የሚችል ትውልድ የማፍራት ጥረቱን የሚመሩ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል ::
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም መምህራን ከስልጠናው በኅላ የመማር ማስተማር ዘዴውን ጠንቅቀው በማወቅ ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ እታች ማውረድና በሙያ ትምህርት የተሻለ ክህሎትና ተቀራራቢ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች የማፍራት ኃላፊነት እንዳለባቸው አብራርተዋል :: አያይዘውም ሰልጣኞች የስልጠናውን አላማ ዳር ለማድረስ በንቁ ተሳትፎ እንዲከታተሉ አሳስበዋል ::
የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ በበኩላቸው መምህራኑ ወደ ትምህርት ዘርፉ በቅርቡ የተቀላቀሉ መሆናቸውን ገልፀው መምህራኑ በስልጠናው የተግባር ላይ ስራ (CTE) መማር ማስተማር ዘዴ እንዴት መምራት እንዳለባቸውና የክፍል ውስጥ ምዘና ዘዴዎች ላይ የተሻለ እውቀት የሚያገኙበት ይሆናል ብለዋል ::
በማያያዝም ከስልጠናው በኅላ የክፍል ትግበራና ምዘና ሂደት የስራ ላይ ምልከታና ምዘና በማድረግ የስልጠናውን ውጤታማነት ቢሮው የሚከታተል መሆኑን ተናግረዋል :: ሰልጣኞችም የስልጠና ሞጁሎችን በመጠቀም የተግባር ላይ ትምህርት ውጤታማነትን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል ::
ስልጠናው በኮተቤ ትምህርት ዩንቨርስቲ መምህራን የሚሰጥ ሲሆን በሁሉም ክፍለ ከተማ የሚገኙ 157 የ ሁለተኛ ደረጃ የተግባር ላይ ትምህርት መምህራን እየተሳተፉ መሆኑን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc