Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 22, 2025 at 01:49 PM
አምስተኛው ዙር የምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ። (የካቲት 15/2017 ዓ.ም) ውድድሩ ከአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞችና ከሶስቱ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ተማሪዎቹ ቀደም ሲል በየክፍለ ከተማው በነበሩ ተመሳሳይ የምስለ ችሎት የማጣሪያ ውድድሮች አሸናፊ ሆነው ለዛሬው ውድድር መቅረባቸው ተገልጿል። የምስለ ችሎት ውድድሩ ከሽግግር ፍትህ ም ሶሶዎች እና አተገባበር ጋር በተገናኘ በዘርፉ ባለሙያዎች የተዘጋጁ ጥያቄዎችን መሰረት አድርጎ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባር መርሀግብር መሻሻልና የተማሪ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ባይሳ ፀጋዬ አስታውቀዋል። ባለሙያው አያይዘውም ዛሬ ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች መካከል 8ቱ ትምህርት ቤቶች በቀጣይ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር በሚደረግ ተመሳሳይ ውድድር እንደሚ ሳተፉ ጠቁመው በስምንቱ ተቋማት መካከል በሚደረገው የምስለ ችሎት ውድድር አሸናፊ የሚሆነው አንድ ትምህርት ቤት ከተማ አስተዳደሩን ወክሎ በፌደራል ደረጃ በሚካሄድ ተመሳሳይ ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆን አመላክተዋል። በዛሬው የማጣሪያ ውድድር እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ 1ኛ፣ ብርሀን የአይነስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ እንዲሁም ገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 3ኛ በመሆን ከሌሎች አምስት ትምህርት ቤቶች ጋር በመሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments