Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 24, 2025 at 06:42 AM
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (የካቲት 17/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ የስነጽሁፍና የሀገር በቀል እውቅት መምህር በሆኑት በዶ/ር ገመቹ ዳዲ የአመራርነት ጥበብ በትምህርት ሴክተር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እውቀታቸዉን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአመራርነት ጥበብ ለስራ ለውጤታማነት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉ በመጥቀስ የቀረበዉ ሰነድ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች በሰራ ሂደት ውስጥ የሚያከናውናቸዉን ጉዳዮች ሊያዩበት የሚገባውን የእይታ አድማስ ያሰፋና እውቀትን ያስጨበጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments