
Addis Ababa Education Bureau
February 24, 2025 at 02:17 PM
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት 10ኛውን የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር መክፈቻ ፕሮግራም አካሄደ።
(የካቲት 17/2017 ዓ.ም) በስፖርታዊ ውድድሩ መክፈቻ መርሀግብርሩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ተማሪዎች፣መምህራን፣ርዕ ሳነ መምህራን እንዲሁም የትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች የተገኙ ሲሆን በክፍለ ከተማው የሚገኙ ወረዳዎች በቅደም ተከተል በመሆን የተለያዩ ትርኢቶችን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ አቶ አሊ ከማል በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስፖርታዊ ውድድሩ "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ፣ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን" በሚል መሪ ቃል በከተማ ደረጃ በመምህራን እና ተማሪዎች መካከል በመካሄድ ላይ መሆኑን ጠቁመው በትምህርት ተቋማት የሚደረግ የስፖርታዊ ውድድር በአካልና አዕምሮ የዳበረና ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ቢሮው ውድድሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በበኩላቸው ከጥር 25/2017ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ቤቶችና በወረዳ ደረጃ ሲካሄድ በነበረ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ለዛሬው መርሀግብር መቅረባቸውን ገልጸው በክፍለ ከተማ አሸናፊ የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች በከተማ ደረጃ በሚደረግ ተመሳሳይ ውድድር ክፍለከተማውን ወክለው የሚካፈሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በመምህራን እና ተማሪዎች መካከል የሚደረግ ስፖርታዊ ውድድር ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ የውድድሩ ተሳታፊ ስፖርተኞች ውድድሩ የሚፈልገውን መርህ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው የክፍለ ከተማው የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልማ አስገንዝበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc