
Addis Ababa Education Bureau
February 24, 2025 at 02:29 PM
"የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን!" በሚል መሪ ሀሳብ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ በመንግስትና በግል ትቤቶች የስፖርት ሊግ ውድድር ተጀመረ።
(የካቲት 17/2017 ዓ.ም) የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ 14 ቀናት የሚቆይ የስፖርት ሊግ ውድድርን አስጀምራል።
በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ የክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ዲሪባ፣ የክ/ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ብሩክ ዘርጋ፣ የዘርፍ የወረዳ ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የስፖርቱ ቤተሰብ፣ መ/ራንና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ዲሪባ በማስጀመርሪያ መርሀ-ግብር ንግግራቸው የስፖርታዊ ውድድሮች የትምህርት ማህበረሰብንና የተማዎችን አብሮነት፤ ፍቅር፣ መተሳሰብንና መዠየመተዋወቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አመላክተው፣ ውድድሩ መምህራን በ5 የውድድር ዘርፎችና ተማሪዎች በ10 የውድድር ዘርፎች ከየካቲት 17/2017 እስከ 30/2017 ዓ.ም የሚቆይና ውድድሩ በሰላም እስኪጠናቀቅ ሁሉም ተሳተፊዎች የበኩላቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ዘርጋ በበኩላቸው ስፖርት ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ ለማፍራት ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመው፤ የስፖርቱ ቤተሰብና ተወዳዳሪ አካላት ውድድሩ በጥብቅ ዲሲፒሊን መመራት እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
በመጨረሻም የክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት የስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪ አቶ ሲሳይ ተሰማ በንግግራቸው ውድድሩ የአሸናፊዎ አሸናፊ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ8 ክላስተርና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በክ/ከተማ ደረጃ በ2ቱም ፆታ ሆኖ በመምህራንና በተማሪዎች የእርስ በእርስ የጥሎ ማለፍ እንደሆነ ገልፀው፤ ትውልዱ ስፖርታዊ ውድድሮችን ባህል አድርጎ ማስቀጠል እንደሚገባው መግለጻቸዉን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc