Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 24, 2025 at 04:54 PM
ከግል ትምህርት ተቋማት ጋር በዕውቅና ፍቃድ እድሳት ማከናወኛ ቼክሊስት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ (የካቲት 17/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን በ2017 ዓ.ም በከተማ አሰተዳደሩ ከሚገኙና ዕውቅና ፍቃድ እድሳት ከሚደረግላቸው የግል ትምህርት ተቋማት ጋር በተከለሰ ቼክሊስት ላይ ግብዓትን ለመስብሰብና ለማዳበር ያለመ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ስራ የሁላችንንም የጋራ ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅና በጋራ የሚሰራ ለጋራ ውጤት የምንታትርበት ነው ፤ ለዚህም የግል ት/ቤቶች ያላችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የእውቅና ፍቃድ እድሳት ተቋማት የትምህርት አሰጣጥን መሰረታዊ የሚባሉ ደረጃዎች ማሟላታቸውን፣ የምንፈልገውን ዜጋ በመቅረጽ ሂደት ውስጥ ተቋማዊ ብቃታቸውን በየጊዜው የሚፈተሽበት መስፈርት በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ነው ብለዋል፡፡ አቶ ኢዘዲን ሙስባህ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው መንግስት ትምህርትን ለዜጎቹ ተደራሽ ለማድረግ መጠነ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ትምህርት ተደራሽ ሲደረግ ጥራቱን ጎን ለጎን ለማስጠበቅ የትምህርት ተቋማት ስታንዳርዱን ባሟላ መልኩ በክትትል ይረጋገጣል፡፡ እነዚህ ተግባራት ሲከናወኑ ከትምህርት ተቋማትና ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱና መነጋገሩ የትምህርትን ጥራት በተሻለ መንገድ ለማስጠበቅ የሚያስችል ይሆናል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥራት ዘርፍ ሃላፊ እንደተናገሩት ከግብአትና ከአደረጃጀት አኳያ ተቋማት ብቁ ሆነው መደራጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ብቁ የሆኑ ተቋማት ደግሞ ብቁ የሆነ ትውልድን ማፍራት ላይ የራሳቸው የሆነ ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው በዚህ ደረጃ እየተሰራ መሆኑን አውስተው፤ የዛሬው የውይይት መድረክ የእውቅና ፍቃድ እድሳት ለማድረግ በተከለሰ ቼክሊስት ላይ በጋራ ውይይት በማድረግና ግብአቶችን በመሰብሰብ በቀጣይ ቼክሊስቱ ከነማናበቢያው ለትምህርት ተቋማቱ እንደሚላክ ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ አቶ ዳዊት ግዛው የአጠቃላይ ት/ት የእውቅና ፈቃድና እድሳት ቡድን መሪ የ2017 ዓም የእውቅና ፍቃድ እድሳት ቼክሊስት ይዘት የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተቋማት ሃላፊነቶች በሚል ርዕስ እንዲሁም ባለስልጣኑ አገልግሎቱን ዲጂታል ለማድረግና ተቋማት በሲስተሙ ላይ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር የተሰራው ሲስተም በባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ሃብታሙ ታምራት እና ሲስተሙን በሰራው ድርጅት ተወካይ አማካኝነት ገለጻ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከቤቱ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments