
Addis Ababa Education Bureau
February 25, 2025 at 02:40 PM
የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት 10ኛውን የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በቦሌ ህብረተሰብ ትምህርት ቤት በሚገኘው የስፖርት ሜዳ በድምቀት አስጀመረ።
(የካቲት 18/2017 ዓ.ም) በስፖርታዊ ውድድሩ መክፈቻ መርሀግብር የክፍለ ከተማውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ተማሪዎች፣መምህራን፣ርዕ ሳነ መምህራን እንዲሁም የትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች የተገኙ ሲሆን በመክፈቻ ስነስርአቱ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቅደም ተከተል የተለያዩ ትርኢቶችን አቅርበዋል።
አቶ መስፍን ታደሰ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስፖርታዊ ውድድሩ "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ፣ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን" በሚል መሪ ቃል በትምህርት ቤት ደረጃ በመምህራን እና ተማሪዎች መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚካሄደው የጥሎ ማለፍ ውድድር መብቃቱን ጠቁመው በትምህርት ተቋማት የሚደረግ የስፖርታዊ ውድድር በአካልና አዕምሮ የዳበረና ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል መርሀ ግብር በመሆኑ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
የቦሌ ክፍለከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መስፍን ሀይሌ በበኩላቸው በትምህርት ቤት ደረጃ የሚካሄድ ስፖርታዊ ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የውድድሩ ተሳታፊ ስፖርተኞች ውድድሩ ለሚፈልገው የስፖርታዊ ጨዋነት መርህ በአግባቡ ተገዢ በመሆን የስፖርታዊ ውድድሩ አላማ እንዲሳካ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
በውድድሩ የመክፈቻ ፕሮግራም በወረዳ 12 እና ወረዳ 13 በሚገኙ መምህራን መካከል የእግር ኳስ ጫወታ ተካሂዷል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc