Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 26, 2025 at 01:19 PM
የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት 10ኛውን የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በድምቀት አስጀመረ። (የካቲት 19/2017 ዓ.ም) በስፖርታዊ ውድድሩ መክፈቻ መርሀግብር የክፍለ ከተማውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ተማሪዎች፣መምህራን፣ርዕ ሳነ መምህራን እንዲሁም የትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች የተገኙ ሲሆን በመክፈቻ ስነስርአቱ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቅደም ተከተል የተለያዩ ትርኢቶችን በማቅረብ ታዳሚውን አዝናንተዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ወዳጆ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስፖርታዊ ውድድሩ "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ፣ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን" በሚል መሪ ቃል በትምህርት ቤት ደረጃ በመምህራን እና ተማሪዎች መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚካሄደው የማጠቃለያ ውድድር መብቃቱን ጠቁመው በትምህርት ተቋማት የሚደረግ የስፖርታዊ ውድድር በአካልና አዕምሮ የዳበረና ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ዜጋ ለመፍጠር የሚያስችል መርሀ ግብር በመሆኑ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራ አመላክተዋል። የየካ ክፍለከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሀንስ ስዩም በበኩላቸው በትምህርት ቤት ደረጃ የሚካሄድ ስፖርታዊ ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የውድድሩ ተሳታፊ ስፖርተኞች ውድድሩ ለሚፈልገው የስፖርታዊ ጨዋነት መርህ በአግባቡ ተገዢ መሆን እንደሚገባቸው በመግለጽ ጽህፈት ቤታቸው ስፖርታዊ ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በኮከበ ጽበሀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የበነበረው የመክፈቻ መርሀግብር በክፍለ ከተማው በሚገኙት ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ እና በብርሀን ጉዞ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች መካከል የእግር ኳስ ጫወታ ተካሂዷል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments