Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 26, 2025 at 01:44 PM
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት አመታዊ ስፖርት ሊግ ውድድር መክፈቻ መርሃ ግብር አካሄደ:: (የካቲት 19/2017 ዓ.ም) የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የ2017 ዓ.ም አመታዊ የተማሪዎችና መምህራን የስፖርት ውድድር መክፈቻ መርሃ ግብር አካሂዷል :: የአራዳ ከፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘሁ በወቅቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኛ ለማፍራትና ተማሪዎች በአካልና በአእምሮ ንቁ ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ያደርጋል ብለዋል:: አፈ ጉባኤው በንግግራቸው ቢሮው ለስፖርታዊ ውድድሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ለስፖርቱ ውጤታማነት የራሱን አሻራ እንደሚያሳርፍ ገልፀው በክፍለ ከተማው ስም ምስጋና አቅርበዋል:: ተወዳዳሪዎችም የተሻለ ውጤት አምጥተው ወደ ቀጣዩ ደረጃ እንዲሻገሩ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል:: በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ተማሪዎች በመልካም ስነምግባር የታነፁና በስፖርት የዳበረ አቅም ያላቸው ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ስፖርታዊ ውድድሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ አክለውም ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኛ የማፍራት ስራውን ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልፀው ውድድሩ በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል :: የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ደበሌ በበኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞች ከማፍራት ባላፈ ዘመኑ ከሚጠይቀው ሳይንሳዊ የስፖርት እውቀት ያላቸውን መሪዎች ማግኘት እነደሚያስችል አብራርተዋል:: በክፍለ ከተማው የተጀመረው ስፖርት ሊግ ውድድር "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን!" በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተነግሯል :: በመክፈቻ መርሃ ግብሩ የአራዳ ክፍለ ከተማ አፈጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘሁ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ደበሌ ፣ የክፍለ ከተማው የመምህራን ማህበር ኃላፊዎችና ወ.ተ.መ ሰብሳቢዎች ተገኝተው ስፖርታዊ ውድድሩን አስጀምረዋል:: ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments