Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
February 26, 2025 at 02:31 PM
በጉለሌ ክፍለ ከተማ 10ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች የስፖርት ሊግ ውድድር መካሄድ ጀመረ። (የካቲት 19/2017 ዓ.ም) ''በትምህርት ቤቶች የስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን ''በሚል መሪ ቃል ዓመታዊ የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተደርጓል። በመክፈቻው ዕለት በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ መርሃ ግብር መሠረት የሴቶች እግር ኳስ እንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጀ ት / ቤት የመድሃኒዓለም 2ኛ ደረጀ ት/ቤት አቻውን 8ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ለከተማ አቀፍ ውድድር ጉለሌን ወከሎ የሚሳተፍ ይሆናል :: ውድድሩ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ተገልጿል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments