Addis Ababa Education Bureau
Addis Ababa Education Bureau
March 1, 2025 at 08:23 AM
የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሰጠ። (የካቲት 22/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በተሻሻለው የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ(ተሙማ)ማዕቀፍ፣በተጽኖ ፈጣሪ የትምህርት ቤት አመራር እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን የእንግሊዘኛ ቋንቋን ኦን ላይን ለማስተማር ካዘጋጀው ፖርታር ጋር በተገናኘ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመምህራን ልማት ምክትል ርዕሳነ መምህራን እና ለክፍለ ከተማ የመምህራን ልማት ባለሙያዎች መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ የስልጠናው ተሳታፊዎች በተሻሻለው የተከታታይ ሙያማሻሻያ(ተሙማ)ማዕቀፍ ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው በየትምህርት ቤቱ ማዕቀፉን በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችሉ ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመው ከተጽኖ ፈጣሪ የትምህርት ቤት አመራር ጽንሰ ሀሳብ ጋር በተገናኘም በየተቋማቱ ብቁና የተሻለ የትምህርት ቤት አመራር ለመፍጠር የሚያስችል የስልጠና መርሀግብር መሆኑን አመላክተዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘውም ትምህርት ሚኒስቴር ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን በቀላሉ ኦን ላይን መማር እንዲችሉ ያዘጋጀው ፖርታር የመማር ማስተማር ስራውን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ተማሪዎች በቀላሉ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን ማሳደግ የሚያስችል ተግባር መሆኑን በመግለጽ ዳይሬክቶሬቱ በቀጣይ በየትምህርት ቤቱ በሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ስልጠናው ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacaebc

Comments