ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 14, 2025 at 01:12 PM
የካቲት 7 2017 የአምቡላንሶችን መልክ እየቀየሩ ለሌላ አላማ የሚያውሉ አመራሮች አሉ ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተናገረ፡፡ በክልሉ በዚህ ዓመት ብቻ 40 እናቶች በጤና ጣቢያዎች ሲወልዱ #ህይወታቸው አልፏል ተብሏል፡፡ በመንግስት የጤና ተቋማት ህገ ወጥ የመድሀኒት ዝውውርም እንደሚፈጸም ተነግሯል፡፡ ይህ የተነገረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ባለበት ወቅት ሲሆን ጉባኤው በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ሪፖርቶች በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት ቀርበዋል፡፡ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የለ #ኮሪደር_ልማት ተብሎ መንገድ ዳር የደረሱ ቤቶች ዳግም በጭቃ እየተገነቡ እንደሆነም በጉባኤው ተነስቷል፡፡ ከዘህ በተጨማሪወም በክልሉ ለመምህራን እና የትምህርት አምራሮች ምዘና ተደርጎ፣ በሂሳብ፣ በእንግሊዝኛ፣ በኢስቴቲክስ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች አንድም መምህር ማለፍ አልቻልም ተብሏል፡፡ በትምህርት ግብዓቶች መሟላት ዙሪያ ግን የተሻለ ውጤት መመዝገቡ ተነግሯል፡፡ ጎዳና ተዳዳሪዎች፣ #ሴተኛ አዳሪዎች፣ ለምኖ አዳሪዎች፣ ስልጠና ሰጥቶ ወደስራ እንዲገቡ ለማድረግ የተሰራ ቢሆንም ካለው ቁጥር አንጻር ግን አነስተኛ ነው ተብሏል፡፡ በተለይ በአንዳንድ የክልሉ ዞኖች ላይ ባልተለመደ መልኩ በየጎዳናው የሚታዩ እናቶች እና ህጻናት እየበዙ ነው ተብሏል፡፡ በክልል በተለያዩ አካባቢዎች ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መኖሩም በጉባዬው ወቅት ተነስቷል፡፡ በተለይ አርብቶ አደር አካባቢዎች የሴቶች ግርፋት እያገረሸ እንደሆነም በቋሚ ኮሚቴዎቹ ተነግሯል፡፡ ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments