
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 14, 2025 at 02:55 PM
የካቲት 7፣2017
በዋግኽምራ ዞን አራት ወረዳዎች ባጋጠመው የምግብ እጥረት ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል፡፡
በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ወረዳዎች 46,000 ሰዎችም ወደ አካባቢው አጎራባች ከተሞች ተሰደዋል ተብሏል።
እነዚህ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያአቸው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰደዱ ያደረጋቸው ከፍተኛ የሆነ ዝናብ በመከሰቱ በጎርፍ እና በመሬት መንሸራተት ነው፡፡
በከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ምክንያት ከ46,000 በላይ ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ወድሟል ተብሏል፡፡
ከክልሉ አደጋ ስጋት እየተሰጠ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ አምራች ከነበረው ዳህና ወረዳ ብቻ ከ24,00 በላይ ሰዎች መሰደዳቸውን ሰምተናል።
ጉዳዩ ትኩረት ተነፍጎታል ሲል ከዋግኽምራ አስተዳደር ዞን ተናግሯል፡፡
በአማራ ክልል 2.3 ሚሊዮን ሰዎች የእለት ጉርስ ለማግኘት እርዳታ ጠባቂ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላዩ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r