ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 15, 2025 at 07:17 AM
#የቅዳሜ_ጨዋታ የዛሬ የካቲት 08 2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እናስተዋውቃችሁ፡፡ ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡ ሟሟሻን ተከተሎ በእሸቴ አሰፋ የሚሰናዳው የመቆያ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ የመጀመሪያዎቹ የገነት ጦር ትምህርት ቤት ምልምሎች ስለ ነበሩት በኋላም ጥቁር አንበሳ የሚል ስያሜ ይዘው የፋሽት ኢጣሊያን ጦርን በመፋለም ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ወጣቶች ፣ከዛሬ 90 ዓመት በፊት ለጦር ስልጠና ከየቤታቸው የወጡበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ከባለፈው ሳምንት ቀጣዩን ክፍል ያቀርብልናል፡፡ በቅዳሜ ጨዋታ በእንግዳ ሰዓታችን፤ በሬድዮና ቴሌቭዥን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት ይታወቁ የነበሩት አቶ ግርማ ቸሩ ከመዓዛ ብሩ ጋር የሚያደርጉት ቆይታ ሁለተኛው ሳምንት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡ ድራማ እና የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ (Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡ ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Comments