ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 15, 2025 at 09:12 AM
የካቲት 8 2017 የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ከፌዴራል መንግስት ጋር የማደርገውን ጥረት ምርጫ ቦርድ እያዳናቀፈብኝ ነው ሲል ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ከሰሰ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሃት ባዘዝኩት መሰረት #ጠቅላላ_ጉባኤ ባለማድረጉና ሌሎችም መከወን ያለበትን ተግባራት ባለመፈፀሙ ለመጭዎቹ 3 ወራት ምንም ዓይነት የፓርቲ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ አግጃለሁ ማለቱን ተከትሎ ፓርቲው በሰጠው ምላሽ ነው ቦርዱን የወቀሰው፡፡ #ምርጫ_ቦርድ ባወጣው መግለጫ ህወሃት እንደ አዲስ መመዝገቡን ጠቅሶ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድና አመራሮችን መምረጥ እንዲሁም መተዳደሪያ ደንቡን ጨምሮ የተለያዩ ሰነዶችን ማፅደቅ ነበረበት ብሏል፡፡ ይህን ባለማድረጉ ለ3 ወራት እግድ እንደተጣለበትና በዚሁ ጊዜ ውስጥም የቦርዱን ትዕዛዝ በማክበር ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ለመከወን ለቦርዱ በደብዳቤ ሲያሳውቅና ቦርዱም ይህን ሲያረጋግጥ እግዱን እንደሚያነሳም አሳውቋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ህወሃትን ከፖለቲካ ፓርቲነት እንዲሰርዘው ከትናንት በስቲያ በመግለጫው ማስጠንቀቁ ይታወቃል፡፡ ይህን የምርጫ ቦርድ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ትናንት #ህወሃት ባወጣው መግለጫም ህወሃት እንደ ቀድሞ አቋሙ እንዲቀጥል እንጂ እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ለምርጫ ቦርድ ያቀረብኩት ጥያቄ የለም ብሏል፡፡ ፓርቲው የፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈፃሚ እንዲሆን ከፌዴራል መንግስት ጋር እየሰራ ያለበትን ሂደት ምርጫ ቦርድ ጣልቃ በመግባት እያደናፈቀፈብኝ ነው ብሏል፡፡ ይህም ህጋዊ እንዳልሆነ እና ለሃገርና ለህዝብም የማይጠቅም መሆኑ መታወቅ አለበትም ሲል በመግለጫው ተናግሯል፡፡ የሰላም ስምምነቱ ለመጨረሻ ጊዜ ተፈፃሚ ሆኖ ጉዳዩ እንዲዘጋም ጠይቋል፡፡ የትግራይ ህዝብ ፍላጎት ሰላምና ፍትህ ነው ሲል ገልጾ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ትግራይ ውስጥ እንዲኖርም ለማስቻልም መንግስት የሚስፈልገውን ስራ እንዲሰራ ጥሪ አቀርባለሁ ብሏል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ….. https://tinyurl.com/bdh3tb8x

Comments