
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 17, 2025 at 01:27 PM
የካቲት 10 2017
የሲሚት - ፔፕሲ - ጎሮ እስከ ቦሌ መንገድ ከዛሬ የካቲት 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሳምንታት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ይሆናል ተብሏል፡፡
መስመሩ ለሚቀጥሉት ሳምንታት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆነው የመንገድ ስራው በፍጥነት መጨረስ እንዲቻል ነው ተብሏል፡፡
ስከዚህም የሲሚት - ፔፕሲ - ጎሮ እስከ ቦሌ መንገድ ከዛሬ የካቲት 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሳምንታት ከለሚ ኩራ ክ/ከተማ ከፔፕሲ - ጎሮ እና ከጎሮ - ፔፕሲ መንገድ በሁለቱም እቅጣጫ መንገዱ የሚዘጋ እንደሚዘጋ ተነግሯል፡፡
በመሆኑ ከፒፕሲ ወደ ጎሮ የምትሄዱ አሽከርከሪዎች በጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ ኢንዱስትሪ መንደር ቦሌ ወረዳ 11 በኩል ጎሮ የሚያገናኝ መንገድ ስላለ እሱን እንድትጠቀሙ፤ እንዲሁም ከጎሮ ወደ ፒፕሲ የምትመለሱ በ ጃክሮስ - ፊጋ- ሳሊተምህረት ወደ ዋና መስመር በመግባትና ሌሎችንም አማራጭ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ተጠቀሙ ብለለሏል የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፡፡
የሲሚት -ፔፕሲ- ጎሮ እስከ ቦሌ መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2ተኛው ዙር እየለሙ ካሉት የኮሪደር ልማት መስመሮች መካከል አንዱ ነው፡፡