ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 19, 2025 at 01:52 PM
የካቲት 12 2017
የጥራት ደረጃቸው አልተሟላም፣ ማን እንዳመረታቸውም አይታወቅም ስለዚህም አትጠቀሟቸው የሚሉ መልዕክቶችን እንሰማለን፡፡
ምርቶቹ ግን ከገበያ ሲሰበሰቡም ሆነ አጥፊዎቹ ሲቀጡ አይታይም፡፡
ምርቱም ስሙን እና መልኩን ቀይሮ ገበያ ላይ ሲውል ይታያል፡፡
ቁጥጥር የሚደረገው እንዴት ነው? የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን ጠይቀናል፡፡
አቶ ሙላቱ ተስፋዬ የባለስልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽን እና የህግ ማስፈፀም ስራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
እሳቸውም ባለስልጣኑ የተበላሹና የምርት ጥራት ችግር ያለባቸውን ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ ህብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው መረጃ እየሰጠ ቢሆንም አንዳንድ ምርቶችን ስማቸውን እየቀየሩ ወደ ገበያ ያወጧቸዋል ብለዋል፡፡
ይህን የሚያደርጉ አምራቾችንም ሆነ አከፋፋዮችን ማወቅ ባለመቻላችን በምርቶች ላይ ብቻ እርምጃ እንድንወስድ ተገደናል ይላሉ፡፡
አቶ ሙላቱ በባለስልጣኑ በኩል እንዳይሸጡ የተከለከሉ ምርቶች ሌላ ስም በመስጠት ዳግም ወደ ገበያ በሚያውሉ አምራቾችም ሆነ አከፋፋዮች እርምጃ ለመውሰድም ድርጊቱን የሚፈፅሙ አካላት ባለመታወቃቸው እርምጃ ለመውሰድ እክል ሆኖብናልም ሲሉ ነግረውናል፡፡
ለመሆኑ የተከለከሉ ምርቶችን ታች ለህብረተሰቡ በሚያቀርቡ ችርቻሮ ነጋዴዎች ላይ ለምን እርምጃ አይወሰድም? ብለን ለአቶ ሙላቱ ላነሳንላቸው ጥያቄ በህጉ መሰረት የተከለከሉ ምርቶችን የሚያመርቱም ለገበያ የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ሆነ አምራቾች እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ቢቀመጥም እስካሁን አልተተገበረም በቀጣይ ግን የታገዱ ምርቶችን ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በሚያቀርቡ ችርቻሮ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወድባቸዋል ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/y5shpvbh
ፍቅሩ አምባቸው