ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 21, 2025 at 01:43 PM
የካቲት 14 2017 በአዲስ አበባ በያዝነው ሳምንት የእሳት ቃጠሎን ጨምሮ የተለያዩ አራት ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል ተባለ፡፡ በ5 የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ላይ ካጋጠመ መታፈን ውጭ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ የለም ተብሏል፡፡ ሳምንቱ እንዴት አለፈ ስንል የጠየቅነው የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤ በሳምንቱ በአዲስ አበባ በንብረት ላይ ጉዳት ያስከተሉ 3 የእሳት አደጋ እንዲሁም በአሳንሰር ብልሽት ምክንያት 1 አደጋ መድረሱን ነግሮናል፡፡ የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በቦሌ አካባቢ ባለው ዋሪት ህንፃ የአሳንሰር ገመድ ተበጥሶ የ7 ዓመት ህፃንን ጨምሮ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነግረውናል፡፡ በተጨማሪም በሳምንቱ በኮልፌ፣ በመካኒሳና በሸገር ከተማ አጃምባ አካባቢ 3 የእሳት አደጋዎች ተከስተዋል፡፡ በአደጋዎቹ እሳቱን ለማጥፋት ሰዓታትን ከፈጁ ጥረቶች በኋላ እሳቱን ማጥፋት ቢቻልም በተለይ በኮልፌ አካባቢ የደረሰው አደጋ ከበድ ያለ ነው ያሉን አቶ ንጋቱ፣ ከባድ የንብረት ጉዳት ደርሷል፤ በ5 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ላይ የመታፈን ጉዳት እንደደረሰና በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አንደሌለም ጠቁመዋል፡፡ በከተማዋ ያሉ የህንፃ ባለቤቶችና አገልግሎት ሰጪዎች የህንጻዎቻቸው አሳንሰሮች ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ የአደጋዎቹ መንስኤና በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እተጣራ መሆኑን የተቀሱት አቶ ንጋቱ፤ያለንበት ነፋሻማ የአየር ንብረት ለእሳት አደጋ መከሰት ምቹ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን ብለዋል፡፡ አርሶ አደሮች ቆሻሻን በማቃጠል ለማስወገድ ሲሞክሩ በማሳዎች እና በደን በተሸፈኑ ከፍታ ቦታዎች የሰደድ እሳት ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ይደረግ ተብላችኋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ …. https://tinyurl.com/wcyd49ht ምንታምር ፀጋው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q 📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il 📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r

Comments