
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 21, 2025 at 05:29 PM
የካቲት 14 2017
በኢትዮጵያ ቡናን እሴት ጨምሮ ከመላክ ይልቅ በጥሬው መላክ የተለመደ ነው።
ይህ መሆኑ ደግሞ ሀገሪቱ ማግኘት ይገባት የነበረውን የውጭ ምንዛሪ እያሳጣት እንደሆነ ይነገራል።
ችግሩን ተረድተው ቡናን እሴት ጨምረው ለተቀባይ ሀገራት የሚልኩትም በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።
ከነሱ ውስጥ አንዱ የሆነው ኢቲኮፍ ቴስት ትሬዲንግ የተሰኘ ተቋም ቡናን በተሻለ መንገድ እሴት ጨምሬ ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ተሰናድቻለሁ ብሏል።
ለመጠጣት ዝግጁ የሆኑ የቡና ምርቶችን በራሱ ፋብሪካ አሰናድቶ ያቀርባል የተባለ ሲሆን ለአንድ ሰው በሚበቃ መልኩ ተሰናድቶ መጠቀም እንዲችል ተደረጎ ተዘጋጅቷልም ተብሏል፡፡
እነዚህ ምርቶችን ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ለውጭ ማህበረሰብ፣ ኤምባሲዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ለተለያዩ አየር መንገዶች፣ ለሆቴሎች እና ለሌሎችም ተቋማት ለማውረብ ውጥን እንዳለው ተነግሮለታል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... https://tinyurl.com/275pea5x
ፋሲካ ሙሉወርቅ