
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 21, 2025 at 09:31 PM
#የቅዳሜ_ጨዋታ
የነገ የካቲት 15 2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡
ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡
ሟሟሻን ተከተሎ በእሸቴ አሰፋ የሚሰናዳው የመቆያ ዝግጅት ይቀርባል፡፡
ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ የመጀመሪያዎቹ የገነት ጦር ትምህርት ቤት ምልምሎች ስለ ነበሩት በኋላም ጥቁር አንበሳ የሚል ስያሜ ይዘው የፋሽት ኢጣሊያን ጦርን በመፋለም ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ወጣቶች ፣ከዛሬ 90 ዓመት በፊት ለጦር ስልጠና ከየቤታቸው የወጡበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ሶስተኛውን ክፍል ይነግረናል፡፡
በቅዳሜ ጨዋታ በእንግዳ ሰዓታችን፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመሪያው ጉባኤ በተካሄደበትና የድርጅቱ ቻርተር በተፈረመበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ፣ በወቅቱ የነበሩ 4 የሀገራችን ከፍተኛ የመንግስት ተወካዮችና ባለሞያዎች ድርጅቱ 50ኛ ዓመቱን ሲያከበር ያጫወቱንን ዘጠኝ ሰዓት ላይ ታደምጣላችሁ።
ድራማ እና ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡
ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!