ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 23, 2025 at 10:44 AM
የካቲት 16 2017 ኢትዮ ቴሌኮም በደሴና በኮምቦልቻ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ። የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱ በይፋ መጀመሩ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እንዲበረታ ያግዛል ብለዋል። ዓለም የደረሰበት ይህ 5ተኛው ኔትወርክ አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች በኢኮኖሚው እንዲራመድ ያግዛል ተብሏል። ትምህርት በኦንላይን ተቀላጥፎ ተማሪም መምህሩም ቀለም በቀላሉ እንዲፈስላቸው ያግዛቸዋል መባሉን ሰምተናል። ጀማሪ የንግድ ተቋማትም የስራ እድል ፈጠራቸው ወደፊት እንዲጓዝላቸው ይህ አገልግሎት እንደሚጠቅማቸው ተሰምቷል። ደሴ፣ ደሴ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ፣ ሉሲ ሆቴልና ደሴ ሙዚየም አካባቢዎች ይህ የ 5ጂ አገልግሎት ሽፋን ተዘርግቶላቸዋል ተብሏል። በተመሳሳይ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አካባቢዎች ይህው አገልግሎት ተወስዶላቸዋል መባሉን ሰምተናል። የመንግስት ተቋማት አሰራራቸው እንዲዘምንላቸው ጤና፣ ግብርና የተጣለበት ተስፋ እንዲሰምርለት ትምህርት ማኑፋክቸሪንግ  የተሻለ እንዲሆኑ ማዕድን፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝሙም አለም የደረሰበት ደረጃ እንዳይቀርባቸውና በዲጅታል ኢኮኖሚው የተሻለ እንዲያዋጡ አገልግሎቱ በብርቱ ያግዛቸዋል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም የ 5ጂን አገልግሎት በ14 ከተሞች  እንዳስጀመረ ይታወቃል። ኩባንያው ከቀናት በፊት የናይጄርያውን ኤምቲኤን በመቅደም ከአፍሪካ በግዝፈት ቀዳሚ የቴሌኮም ኦፕሬተር መሆኑ ይታወቃል። ተህቦ ንጉሴ

Comments