ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 26, 2025 at 10:07 AM
የካቲት 19 2017 የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ በ2013 ዓ. ም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮዽያ 70.2 ሚሊዮን የዳልጋ ከብት፣ 42.9 ሚሊዮን በጎች፣ 52.5 ሚሊዮን ፍየሎች እና 8.1 ሚሊዮን ግመሎች አሏት፡፡ ይህ ቢሆንም ከዘርፉ እያገኘች ያለቸው ገቢ ካላት የእንስሳት ሀብት ብዛትና ከያዘችው ደረጃ ጋር አይመጣጠንም፡፡ የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ህጋዊ ላኪዎችን እያማረረ መሆኑንም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ተናግሯል። በዘርፉ ሲያጋጠሙ የነበሩ ችግሮችም ኢትዮጵያ በእንስሳት ብዛት በአፍሪካ ቀዳሚ 70.3 ሚሊዮን የሚገመቱ የቀንድ ከብቶች፣ 95.4 ሚሊዮን በግና ፍየሎች እንዲሁም 8.1 ሚሊዮን ግመሎች መገኛ ብትሆንም ዘርፉ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ፈተናዎች ሲገጥሙት ቆይቷል። ከእነዚህም ችግሮች መካከል ቀንድ ከብቶች የት እንዳሉ ለመከታተል ያለው እጅ ማጠርና ልማዳዊ የእንስሳት መለያ ዘዴ አንደኛው መሆኑ ተሰምቷል። ብዙውን ጊዜም የእንስሳትን ጤናን፣ እንቅስቃሴን እና ባለቤትነት ለመከታተል መንገዱ አሁንም አስቸጋሪ ነው ተብሏል። ይህም የእንስሳት ሀብት አያያዝ ችግር በመሆኑ እንስሳትን ለበሽታ እና ለስርቆት አደጋ እንዲጋለጡ በማድረግ ኢትዮዽያ ለውጭ የምታቀርባቸው የቁም ከብቶች ላይ ከፍተኛ የጥራት ችግር በመፍጠር በአለም አቀፍ ገበያ እንዲወድቁ ያደርጋል ተብሏል። ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/3b9m3w6p

Comments