
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 27, 2025 at 12:51 PM
#ምጣኔ_ሀብት
በአብዛኛው ገበሬው ለፍቶ ካመረተው ምርት ገና ከመዳረሻው ሳይደርስ የሚበላሸው ምርት 40 በመቶ ይሆናል።
ሙዝ አቮካዶ አትክልትና ሌላውም ገበያውና ፈላጊው ሳይገናኝ ቀርቶ የተደከመበት ሁሉ ይበላሻል።
#የአገልግሎት_ጥራት ሲባል ዝም ብሎ በአንድ ጀንበር የሚመጣ አይደለም።
የአገልግሎት ጥራት ሲባል ልፋት፣ ድካም፣ የየእለት ውጣ ውረድና መጠናቀቅ ይፈልጋል።
በየትኛውም መአዘን አገልግሎት በስሩ የስራ ሥነ-ሥርዓትን ማወቅ፤ ለአገልግሎት የሚያስፈልገውን መሳሪያና የተማረውን ሰው ማቅረብ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መታጠቅ ግድ እንደሆነ በዘርፋ የተሰየሙት ይስማሙበታል።
አፈር ተጎልጉሎ፣ ታርሶ፣ ምርት ተመርቶ ተትረፍርፎ ወደ ሚፈለገው ቦታ ካልሄደ ፤ #ገበያ ካላረጋጋ የተረፈውም ወደ ውጭ ካልተላከ ውጤት አያመጣም።
ዛሬ ከኢትዮዽያ ኃላ የተነሱ የአፍሪካ አገሮች ውሃ ጠልፈው፣ መሬት ደልድለው፣ ብርቱካን፣ አቮካዶውን፣ አበባ፣ ሙዙን አትክልቱን ወደ ውጭ በገፍ ይልካሉ።
ይህ የሆነው ጤነኛ የሎጅስቲክስ ሥርዓትና መስመር ስላላቸው እና መንገዱንም ስላወቁበት ነው።
በኢትዮዽያ አበባውን፣ አቮካዶውን፣ ሙዝ፣ ዓሣ፣ ስጋው አትክልቱን ከተመረተበት ቦታ ወደ ገበያ ለማምጣት ለማረጋጋት የሚፈትነው ዋናው ጉዳይ የትራንስፖርት ማጓጓዝና አጠቃላይ የሎጅስቲክስ ችግር ነው።
የተጣጣመ የሎጅስቲክ ሥነ-ሥርአት ከሌለ የተለፋበት ምርት ሁሉ የፀሐይ መጫወቻ፣ የቅዝቃዜ ማሳለፍያ ይሆናል።
ይህ ሁሉ ምርትና ልፋት እንዳይበላሽ የራሱ የሆነ መንገድ እንዳለው አቶ ዳዊት ውብሸት ይናገራሉ።
አቶ ዳዊት ውብሸት በሎጅስቲክስ ረዘም ያለ ልምድ አላቸው፡፡
እሳቸው በአለም አቀፉ የእቃ አስተላላፊዎች ማህበራት ፌዴሬሽን የአየር ጭነት ኢንስቲትዩት ኃላፊ ናቸው።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/s8amxjyv
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r