ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 27, 2025 at 02:03 PM
የካቲት 20 2017
ከዶላር አንፃር የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ የመግዛት አቅም ከጀመረው የቁልቁለት ጉዞ የማቆሚያው መላ ምን ይሆን?
የብር የመግዛት አቅም ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከመቶ በመቶ በላይ ወርዷል፡፡
ገበያ መር ነው የተባለው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የነበረው አንድ የአሜሪካን ዶላር የመሸጫ ዋጋ ከነበረበት 57 ብር ወደ 127 ብር ከፍ ብሏል፡፡
ለሁለተኛ ዙር የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ እለት ብሄራዊ ባንክ በገበያው ላይ ያለውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ለማሻሻል በሚል በጨረታ የሸጠው 60 ሚሊዮን ዶላር የተገዛበት የአንድ አሜሪካን ዶላር አማካኝ ዋጋም የብር የመግዛት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ጊዜ መንሸራተቱን በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል፡፡
በመጀመሪው ዙር ብሄራዊ ባንክ አውጥቶት በነበረው ጨረታ በአማካኝ አንድ የአሜሪካን ዶላር የተሸጠበት ዋጋ 107 የነበረ ሲሆን የካቲት 18 ቀን ለሁለተኛ ዙር በቀረበው ጨረታ እና 27 ባንኮች እንደተሳተፉበት በተነገረው ላይ ደግሞ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ135.61 ብር ተሽጧል፡፡
ለመሆኑ ከ90 በመቶ በላይ የመሆኑት ባንኮች አንድ የአሜሪካን ዶላር 135.61 ተጫርተው የገዙት ገንዘብ ኖሯቸው ነው? አትርፈው ለመሸጥስ ግዢ አግኝተው ነው? የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም የመድክም ጉዞ ማብቂውስ የት ነው ?
ሁለት የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያዎችን ጠይቀናል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ ሽያጭ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ እያገኝ መሆኑን እና በዛው ልክ ደግሞ ወርቅ ለመግዛት ከፍተኛ ብር ወደ ገበያው እያፈሰሰ ስለሆነ ወደ ገብያው የፈሰሰው ብር ደግሞ የዋጋ ንረቱን እንዳያባብስ ዶላርን ለባንኮች በጨረታ በማቅረብ ከገበያው ላይ ብርን ለመሰብሰብ እና ገበያውን ብር ለማስራብ ብሄራዊ ባንክ ዶላርን ለጨረታ እንዳቀረበ የፋይናስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያ እና አማካሪው አቶ ጥላሁን ግርማ ያስረዳሉ፡፡
አቶ ጥላሁን ለባንኮች በጨረታ የተሸጠው 60 ሚሊዮን ዶላር ባንኮች ያለባቸውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በማስረዳት በሀገሪቱ ካሉ ባንኮች ውስጥ ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መሳተፋቸው እና ዝቅተኛ ሀብት ያላቸው ባንኮች የተሻለ የሃብት አቅም ካላቸው ባንኮች ጋር እኩል ተወዳድረው መጫረታቸው ግን ጤናማ አካሄድ አልመሰለኝም ብለዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ….. https://tinyurl.com/2s4b429s
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r