
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 27, 2025 at 05:26 PM
#ምጣኔ_ሀብት
ህግ ሲቀያየር ደንብና ፖሊሲ አልረጋጋ ሲል ምን ሊነግረን ይችላል?
መንግስት አቅም አለው፣ ጉልበት አለው ሲባልስ ምን ማለት ነው?
የማህበረሰብን ሰላም የሚረብሽ ህግና ደንብ መመሪያም ሆነ ተፈፃሚ ላይሆን የሚችል ህግ ምን ስጋትና መደናበር በኢኮኖሚው ውስጥ ያመጣል?
የንብረት ማስመለስ አዋጅ ወደ ስራ ሲተረጎም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲኖረው ካልተደረገ ጣጣው ብዙ እንደሆነ ስጋት አለ።
በልማድና በዘልማድ ሲነግድ የኖረ ህዝብ ይህ ይመጣብኛል ብሎ አልኖረምና ደረሰኝም ማስረጃም ላያቀርብ ይችላል።
ይህ ማለት ግን ያፈራው ንብረት የወንጀል ፍሬ ነው ማለት ፈፅሞ አይደለም ይባላል።
ለመሆኑ አንድ ግለሰብ እራሱን በራሱ ነፃ ለማድረግ በህግ ዓይን ምን ዓይነት ማስረጃ ሊያቀርብ ይችላል?
የቢዝነስ ሥርዓቱ የንግድ ጠባዩና ሌላውስ ይህን የንብረት ማስመለስ አዋጅ ህግ ተፈፃሚነቱን የት ድረስ ያስጉዘዋል?
አቶ ያዕቆብ በቀለ በሙያቸው የፖለቲካ ኢኮኖሚስት ናቸው ከላይ ላነሳነው ሀሳብ ተጨማሪ ማብራሪያና ምላሽ አላቸው።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/ymnuuwhm
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r