ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 28, 2025 at 08:31 AM
#ምጣኔ_ሀብት ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚው ያግዘኛል፣ ሥርዓትና ደንብ ያስይዝልኛል፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚውንም ሆነ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚውን መንገድ ያጠራልኛል ስትል፤ በየጊዜው ህግና ፖሊሲ ታረቅቃለች አርቅቃም ታስፈፅማለች። አሁን ችግሩ በሚወጣና ህግና ደንብ ክፍተቱን እየፈለጉ ሰላማዊው ዜጋ እንዳይበደል ምን መሳይ ጥብቅ ቁጥጥር እና እግር በእግር ክትትል አለ? ይላሉ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ዘርፍ ተከራካሪዎች። የንብረት ማስመለስ አዋጅ ጋር በተገናኘ በፋይናንስ ማዕዘን ባንክም ድረስ፣ ጉልበት ያለው፣ ህግን በማስጠበቅ ረገድም ታንክም ድረስ ጉልበት ያለው መንግስት፤ ንብረት እስካልተሰወረ ድረስ የወንጀል ፍሬ የሆኑት ንብረቶች እንዴት ይለቀማሉ በሚለው ዙሪያ ስራው ጥብቅ እንደሆነ ይነገራል። በዚህም ሰበብ ከፍተኛ ጉልበት ያለው ወይም ከፍተኛ ገንዘብ የሚገላበጥበት የግዥና ሽያጭ ሥርዓት እንዳይደናበር፣ ኢኮኖሚውም እንዳይደናበር ከፍተኛ ጥንቃቄ መኖር አለበት ይባላል። የህግ ክፍተቱ እየተፈለገ ለከፍተኛ ንጥቂያ እንዳያመራ ከወዲሁ ብዙ ስራ ይጠበቃል። አቶ ያእቆብ በቀለ ከላይ ለተነሱት ሀሳቦች ማብራሪያቸውን ይነግሩናል። አቶ ያእቆብ የፖለቲካ ኢኮኖሚስት ናቸው በፌደራሊዝምና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ረዘም ያለ የስራ ልምድ አላቸው፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/yxk22p69 ተህቦ ንጉሴ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q 📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd 📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s 📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il 📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r

Comments