
ShegerFM 102.1(ሸገር 102.1)
February 28, 2025 at 06:12 PM
#የቅዳሜ_ጨዋታ
የነገ የካቲት 22 2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡
ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡
ሟሟሻን ተከተሎ በእሸቴ አሰፋ የሚሰናዳው የመቆያ ዝግጅት ይቀርባል፡፡
ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ: በአድዋ ጦርነት ወቅት የጦር አበጋዙ ፊት አውራሪ ገበየሁ በጀግንነት ሲዋጉ በጠላት ጦር መትረየስ ተመትተው አድዋ ኪደነ ምህረት በር ላይ በተጋድሎ የታዋደቁበትን 129ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ያስታውሰናል፡፡
በቅዳሜ ጨዋታ በእንግዳ ሰዓታችን፤ በትምህርት አገልግሎት 100 ዓመት የሞላውንና ''TMS'' በመባል ይታወቅ የነበረውን የተፈሪ መኮንን ት/ቤት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ከቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ወ/ሮ የመስራች ፈለቀ፣ ወ/ሮ ቆንጂት ተድላ፣ ሻምበል አርጋው ካብታሙ እና ከካፕቴን ከበደ ወልደፃድቅ ጋር የተደረገውን ጨዋታ 9 ሰዓት ሲሆን ይጀምራል።
ትረካ እና ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡
ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!