ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
February 22, 2025 at 06:11 AM
❗❗#ቅበላ_ምንድን_ነው ?❗❗ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, 🔴👉 ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው:: 🔵👉 ቅበላው መንፈሳዊ ከሆነ በመንፈሳዊ ሕይወት ጸድቶ መዘጋጀት ነው:: መጪው ጾም ከሆነ ለዚህ እንግዳ ንስሐ መግባትን በመጾም በመስገድ በጾሙ ወቅት ለሚፈጸሙ ሥርዓቶች ራስን አዘጋጅቶ መቀበል ነው:: በዚህም ምክንያት ቅበላን በመብል በመጠጥ ሳይሆን ጾምን ሯሷን ጹመው ቅበላ ያደርጉባታል አበው:: 🔴👉 ምክንያቱም በጉጉት የሚጠብቋት የሚጠቀሙባት በዓመት የሚናፍቋትን የጾም እንግዳ ሊቀበሉ ነውና! እንግዳ ሲመጣ እንደ እንግዳው ክብር መዘጋጀት ይገባልና:: እኛ ልጆቻቸው ዛሬ እንደሚታየው እንደነርሱ ባንሆን እንኳ እነርሱ የሰሩትን ሥራ ሠርተን ልንመስላቸው ይገባናል እንጂ መጠጥ ቤቱን ጭፈራ ቤቱን የዝሙት መንደሩን ልናጨናንቅ አይገባም:: 🔵👉 መፅሐፍ ከእንደዚህ ካለ ግብርም መንደርም ራቁ ተለዩ ነው የሚለው። ቅበላ ምግብን በመበቀል አልነበረም አይደለምም:: በጾም እንደ አበው ነው:: መንፈሳዊ ዝግጅትን በማድረግ ነገር ግን ለክርስቲያኖች በማይገባ በመብል በመጠጥ በዝሙት በጭፈራ በዳንኪራ ጾምን መቀበል ነውር ነው:: ኽረ ኃጢአትም ነው። 🔵👉 አንድ መንፈሳዊ ሰው ክርስቶስን ነው የተሸከመው በክርስቶስ ነውና ክርስትናን ያገኘው እና ክርስቲያን መሆን አለበት:: አንድ ክርስቲያን እኔ ክርስቲያን ነኝ እኔ በክርስቶስ ክርስቲያን ነኝ የሚለው በክርስትናው ሲመላለስ ነው። ክርስትና ደግሞ በፍቅር ሕግ ተገዝቶ በሥርዓት መኖር ነው። ሁሉ ተፈቅዶልናል ነገር ግን ሁሉ አይጠቅመንም እንደተባለ። 🔴👉 አብዝቶ መብላትና መጠጣትን በማንኛውም ቀን ቢሆን ለክርስቲያን በዚህ ግብር መታደም መታየትም ማሰብም አይገባም:: በክርስቶስ ደም የከበረን ሰውነት በዝሙት፣ በሥካር፣ በጭፈራ በእንደዚህ ያሉ ግብር ማቆሸሽ የአሕዛብ ሥራ ነው ለክርሲቲያን ግን ተገቢ አይደለም:: ❗👉 ክርስቲያኖች ቅበላቸው በየደብሩና በየገዳሙም ሱባኤ በማሰብ ንስሐ በመግባት የበደልነውን በመካስ የቀማውን በመመለስ በፊት ከሚበላው ከሚጠጣው ቀንሶ በመጥን ብቻ ሳይሆን በዓይነትም ቀንሶ ለመጪው ጾም ይዘጋጃል:: ❗ስለዚህም አብይ ፆምን የካቲት 17 በዕለተ ሰኞ ለመቀበል እስከ የካቲት 16 ዕለተ እሁድ ድረስ መዘጋጀት አለብን ማለት ነው።❗ ❗ፆሙን የፍቅር የሠላም የበረከት ያድርግልን። ፆም ፀሎታችንን ሁሉ እርሱ እንደ ሀጥያታችን ብዛት ሳይሆን እንደ ምህረትና ቸርነቱ ይቀበልልን።❗             ❗#መልካም_ፆም❗ ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።     ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።      ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።   ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም       የካቲት 15 /2017 ዓ.ም                  ሆለታ ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ 🔴👉 በቴሌግራም | Telegram        👇👇👇👇👇👇 https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom 🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp        👇👇👇👇👇 https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w 🔴👉 በዩትዩብ | YouTube       👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@yonastube
🙏 1

Comments