
ዮናስ ቲዩብ - yonas tube
February 24, 2025 at 08:34 AM
❗ጾመ ሕርቃል ለምን ይፆማል ?❗
🔷👉 መቼ ይፆማል ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 የመጀመሪያ የዐብይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል በተጨማሪም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ፆመ ሕርቃል ለምን ተባለ ቢሉ :-
🔷👉 ታሪኩ እንዲህ ነው በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡
🔴👉 መስቀሉን ቢነካው አቃጠለው ከዚያም ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡
🔵👉 በዚያ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ለንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ ይህን ሕግ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡
🔴👉 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና አሸነፈ ነገር ግን መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው መስቀሉን አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ።
🔷👉 ታዲያ እኛም ዛሬ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል የመንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡
🔴👉 በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያናችን ሱባኤ በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ስም ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
❗ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን❗
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 17 /2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #like_follow_share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube
🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16