Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
February 5, 2025 at 06:07 AM
የሳምንቱ #humanrights Concept: የሴት ልጅ ግርዛት ... የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል፣ በአንቀጽ 5 አባል ሀገራት የሴቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣችው መስፈርቶች ጋር የሚጣረሱ ሁሉንም ዐይነት ልማዳዊ ድርጊቶች መከልከልና ማውገዝ አለባቸው። አባል ሀገራት ቅጣትን የሚያስከትሉ ሕጎችን በማውጣት ማንኛውንም ዐይነት የሴት ልጅ ግርዛትን መከልከል አለባቸው። የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና አንቀጽ 566 ላይ የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው። 🔗 https://ehrc.org/?p=31238 #ethiopia🇪🇹 #endfgm #endfemalegenitalmutilation #unite2endfgm #keepwordsafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Comments