Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ WhatsApp Channel

Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ

72 subscribers

About Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ

EHRC is an independent NHRI tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

Similar Channels

Swipe to see more

Posts

Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
6/18/2025, 8:24:08 AM

የሳምንቱ #HumanRights Concept: በትጥቅ ግጭቶች ውስጥ የሴቶች ጥበቃ ... የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 1(በ)፣ 4(2)(ለ) እና 11(1) አባል ሀገራት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉም ዐይነት ጥቃቶችን የሚከለክሉ ሕጎችን ለማውጣት እና ለማስፈጸም ተገቢ እና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው። በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሰላም ጊዜ እንዲሁም በትጥቅ ግጭት ወይም ጦርነት ጊዜ የሚፈጸሙ የጥቃት ድርጊቶችን ያጠቃልላል። አባል ሀገራት በሕዝብ በተለይም በሴቶች ላይ ተጽዕኖ በሚያደርሱ የትጥቅ ግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ደንቦች የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለባቸው። 🔗 https://ehrc.org/?p=33463 #Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Video
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
6/13/2025, 1:45:41 PM

በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ላይ የተካሄደ የባለሙያዎች ውይይት ... በሀገር አቀፍ ደረጃ የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል የተጀመሩ ጥረቶች ውጤት እንዲያስገኙ ኢሰመኮ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረጉን ይቀጥላል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ረገድ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ የባለሙያዎች ውይይት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። ኢሰመኮ ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን አስመልክቶ ባካሄደው ብሔራዊ ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ላይ በዘርፉ ከሚሠሩ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ተቋማት፣ የዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤቶች፣ የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማእከል እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተውጣጥቶ የተቋቋመው የባለሙያዎች ኮሜቴ አባላት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ እና የዴንማርክ ሰብአዊ መብቶች ተቋም ተወካዮች በውይይቱ ላይ በአማካሪነት ተሳትፈዋል። በመድረኩ ፍትሕ ሚኒስቴር በተለያዩ የውይይት መድረኮች በተሰጡ አስተያየቶችና ግብአቶች መሠረት ያሻሻላቸው የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ይዘቶች ለኮሚቴው ቀርበው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል። 🔗 https://ehrc.org/?p=33424 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
6/13/2025, 1:09:21 PM

Regional Meeting on Family Law Reform and Women’s Rights in the Greater Horn of Africa (GHOA) ... The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) participated in the Regional Conference on Revitalizing Advocacy for Family Law Reform and Strengthening Regional Collaboration to Counter Backlash Against Women’s Rights in the Greater Horn of Africa, held in Kampala, Uganda, from May 28-29, 2025. Organized by Strategic Initiative for women in the Horn of Africa (SIHA) and partners of the Africa Family Law Network (AFLN), the conference brought together government representatives, national human rights institutions, scholars specializing in family law, women’s rights organizations, grassroots activists, community and religious leaders, persons with disabilities and influential community actors across GHOA. 🔗 https://ehrc.org/?p=33416 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
6/11/2025, 7:10:48 AM

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሕፃናት ከጉልበት ብዝበዛ የመጠበቅ መብት ... የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1) (መ) ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው። ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 32(2) (ሀ-ሐ) ተዋዋይ ሀገራት በተለይ፡- ዝቅተኛ የቅጥር ዕድሜን ወይም ዕድሜዎችን ይወስናሉ፤ የሥራ ሰዓትንና የቅጥር ሁኔታዎችን በተመለከተ ተገቢውን ደንብ ያወጣሉ፤ ይህ አንቀጽ በሚገባ በሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተገቢ ቅጣቶችን ወይም ሌሎች ክልከላዎችን ያስቀምጣሉ። 🔗 https://ehrc.org/?p=33411 #Ethiopia🇪🇹 #EndChildLabour #KeepWordSafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Video
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
6/10/2025, 9:15:04 AM

ሀገር አቀፍ ውይይት፦ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፕሮጀክት ኤክስፔዳይት ጀስቲስ (Project Expedite Justice, PEJ) ጋር በመተባበር በሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ላይ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። በኢሰመኮ፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻዎች መካከል ያለውን ትብብርና ቅንጅት ማጠናከርን ዓላማ ባደረገው ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሰጪ አካላት ተሳትፈዋል። በውይይት መድረኩ ኢሰመኮን ጨምሮ የሦስት ተቋማት የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳን የተመለከቱ ገለጻዎች፣ መልካም ተሞክሮዎች እና ተግዳሮቶች ቀርበዋል። በኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ፅንሰ ሐሳባዊ ማብራሪያ፣ የሰብአዊ መብቶች ስነዳ ዐይነቶች፣ የስነዳ አስፈላጊነት፣ በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና ማስፋፋት ላይ ኢሰመኮ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚጋሯቸው ጉዳዮች፣ በሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ መካከል ያለው ልዩነት እና አንድነት እንዲሁም ተግባራዊ ሊሆኑ የሚገቡ የሰብአዊ መብቶች መርሖች፣ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ወሰን (scope) እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ገለጻ ተድርጓል። 🔗 https://ehrc.org/?p=33387 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
5/17/2025, 11:57:13 AM

Advancing Peace, Justice and Inclusion Through Strengthened Partnerships and Collective Action ... EHRC took part in the 2025 Sustainable Development Goal 16 (SDG 16) Conference held at UN Headquarters in New York The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) participated in the 2025 SDG 16 Conference held at UN Headquarters in New York under the theme “Advancing Peace, Justice and Institutions for Sustainable Development” on May 12, 2025. The conference convened global leaders and stakeholders from government, civil society, and multilateral organizations to assess progress and define next steps in delivering on Sustainable Development Goal 16 (SDG 16) as a foundation for broader achievement of the 2030 Agenda. The event was co-hosted by the UN Department of Economic and Social Affairs, the Permanent Mission of Italy, and the International Development Law Organization. 🔗 https://ehrc.org/?p=32848 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
5/18/2025, 9:29:24 AM

የሴት ልጅ ግርዛትን አስመልክቶ በሚካሄድ ግልጽ የምርመራ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት ... በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛት እና ተደጋጋሚ ግርዛትን ለማስቆም ማኀበረሰብን ማንቃት፣ ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረግ እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሴት ልጅ ግርዛት ላይ ስለሚያካሂደው ግልጽ የምርመራ መድረክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዓላማ የግልጽ ምርመራ መድረኩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ማሳወቅ እና አስፈላጊ በሆኑ በትብብርና እገዛዎች ላይ መወያየት ነው። በውይይቱ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከአፋር እና ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ፍትሕ ቢሮ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ጤና ቢሮ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የሀዲያ ዞን ሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ፣ የፍትሕ፣ የፖሊስ እና ጤና ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በተጨማሪም በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና የኢሰመኮ የከተማ ጽሕፈት ቤቶች የሴቶች እና የሕፃናት መብቶች ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። 🔗 https://ehrc.org/?p=32857 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
5/16/2025, 1:11:40 PM

83rd Ordinary Session of the African Commission on Human and Peoples’ Rights in Banjul, The Gambia ... EHRC will closely follow the African Commission’s recommendations in response to Ethiopia’s report and monitor implementation The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) delegation, comprising of Chief Commissioner Berhanu Adello, Commissioner for Civil, Political and Socio-Economic Rights Dr. Abdi Jibril and other senior officials, participated in the 83rd Ordinary Session of the African Commission on Human and Peoples’ Rights (African Commission), in Banjul, The Gambia from May 2 to 12, 2025. 🔗 https://ehrc.org/?p=32844 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
5/21/2025, 6:21:21 AM

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሴቶች የጤና መብት ... በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 12 (1) አባል ሀገራት የወንዶች እና የሴቶች እኩልነትን መሠረት በማድረግ የቤተሰብ ምጣኔን ጨምሮ የጤና ጥበቃ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ በጤና ጥበቃ ዘርፍ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን አድልዎ ለማስወገድ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ። የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 14 (2) (ሀ) አባል ሀገራት ለሴቶች በተለይም በገጠር ለሚገኙ የመረጃ፣ የትምህርት እና የግንኙነት መርኃ ግብሮችን ጨምሮ በቂ፣ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ የጤና አገልግሎቶችን ለመስጠት አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ። 🔗 https://ehrc.org/?p=33013 #Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Video
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
5/14/2025, 8:48:24 AM

ሰብአዊ መብቶችን ማስፋፋት፦ በ2017 ዓ.ም. በሦስተኛው ሩብ ዓመት የተሰጡ ስልጠናዎች ... የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከጥር 1 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ፣ በሕፃናት፣ በታራሚዎች፣ በአረጋውያን እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን በተለያዩ ከተሞች ሰጥቷል። በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ የወጣቶችን ሚና ለማሳደግ ያለሙ ስልጠናዎች ከተለያዩ ወጣት ማኅበራት ለተውጣጡ 63 አመራሮች እና አባላት ከየካቲት 10 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. በአርባምንጭ ከተማ እና ከመጋቢት 15 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በሶዶ ከተማ ተሰጥቷል። በተመሳሳይ የማሕበረሰብ እና የሃይማኖት መሪዎችን ትኩረት ያደረጉ በድምሩ 64 ተሳታፊዎች የተሳተፉባቸው ስልጠናዎች ከየካቲት 4 እስከ 6 ቀን 2017 በጅማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ተከናውነዋል። በስልጠናዎቹ ስለ ሽግግር ፍትሕ ጽንሰ ሐሳብ፣ የሌሎች ሀገራት የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮዎች እና በሂደቱ ታሳቢ ሊደረጉ የሚገቡ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች የቀረቡ ሲሆን ክህሎትን የሚያሳድጉ ተግባራዊ ልምምዶች ተካተዋል። በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ ከመጋቢት 1 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል። 🔗 https://ehrc.org/?p=32785 #Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post image
Image
Link copied to clipboard!