
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
February 12, 2025 at 07:37 AM
የሳምንቱ #humanrights Concept: ሴቶችን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማብቃት
...
የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 12(2) እና አንቀጽ 18 (2)(ለ)
አባል ሀገራት፦
በሴቶች ዘንድ ማንበብ እና መጻፍን ለማስፋፋት፣
በሁሉም ደረጃዎችና በሁሉም የትምህርት ዘርፎች በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሴቶች የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለማስፋፋት ዝርዝር አወንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።
አባል ሀገራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ በአዲስና ታዳሽ የኃይል ምንጮች እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ምርምርንና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት፣ በዚሁም ላይ የሴቶችን ተደራሽነት እና የቁጥጥር ተሳትፎ ለማመቻቸት ተገቢውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ ይገባቸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31321
#ethiopia🇪🇹 #womeninscience #idwgs #womeninstem #womeninscienceday #keepwordsafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።