Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
February 17, 2025 at 08:14 AM
የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች ከሴቶች ሰብአዊ መብቶች አንጻር ያላቸውን አተገባበር በተመለከተ የጥናት ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት ... የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች አተገባበር ለሴቶች መብቶች መከበር ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች ከሴቶች መብቶች አንጻር ያላቸውን አተገባበር በተመለከተ ባከናወነው ጥናት ላይ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይት መድረኩ በጥናቱ የተለዩ ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪ አካላት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል። 🔗 https://ehrc.org/?p=31349 #ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Comments