
Ethiopian Human Rights Commission - ኢሰመኮ
February 28, 2025 at 09:11 AM
#ቤኒሻንጉል፦ የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ ውይይት
...
በማረሚያ ቤቶች ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍና የታራሚዎችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብና የተቀናጀ ሥራ ይጠይቃል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት አራተኛው ሩብ ዓመት እንዲሁም በ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት አንደኛው እና ሁለተኛው ሩብ ዓመት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባሉ ሁሉም ማረሚያ ቤቶች በታራሚዎች እና በቀጠሮ እስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ባከናወናቸው የክትትል ሥራዎች የተለዩ ግኝቶች ላይ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በባምባሲ ከተማ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የክልሉ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የፍትሕ ቢሮ ተወካዮች፣ የአሶሳ፣ የካማሺ እና የመተከል ዞን ማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31536
#ethiopia🇪🇹 #humanrightsforall
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።