Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 1, 2025 at 04:47 PM
*በጂቡቲ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፤* በጂቡቲ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር 2ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በኮሚዩኒቲ አዳራሽ በፎቶ ተካሂዷል። በመድረኩም የማህበሩ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ማህበሩ አጠቃላይ በሰራቸው ስራዎች ላይ መሻሻል ያለባቸው እና በቀጣይ መታየት ያለባቸው ነጥቦች ተነስተዋል። በመቀጠል እስከአሁን ማህበሩን ሲያገለግሉ ለነበሩ አመራሮች እውቅና በመስጠት የዕለቱን አዲስ የስራ አስፈፃሚ እና ኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚቴ የምርጫ መርሃ-ግብር ተካሂዷል። በምርጫ ሂደቱ ፍትሀዊ እና ሁሉ ያካተተ ለማድረግ በኮሚቴው በኩል የተወሰዱ ሂደቶችን በማብራራት ዕጩ ተመራጮችን ለመድረኩ ቀርቦ ጸድቋል። በመጨረሻም ምክትል የሚሲዮናችን መሪ ክብር ከበደ ብርሀኑ የሴቶች ማህበሩ አዲስ የተመረጡትን አመራሮች በመደገፍ እና አባላትን በመጨመር ለበለጠ አንድነት በጋራ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Comments