
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
630 subscribers
About Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Official WhatsApp Channel of Ethiopian Embassy to Djibouti
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄኔራል እና የአፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ውይይት አድርገዋል።


ምክትል የሚሲዮኑ መሪ በተገኙበት ከትግራይ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ተደረገ፤ (ሰኔ 14/2017 ዓ.ም) ምክትል የሚሲዮኑ መሪ ክቡር ከበደ አበራ በተገኙበት ከኢትዮጵያ የትግራይ ልማት ማህበር ጽ/ቤት አመራሮች እና በጅቡቲ ከትግራይ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ተደርጓል። ክቡር ከበደ አበራ በመክፈቻ ንግግራቸው ሚሲዮኑ የልማት ማህበሩን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህም በዚህ አደረጃጀት ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማበረታታት ያለመ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። የማህበሩ አመራሮች በበኩላቸው እስከአሁን ኤምባሲው ማህበሩ እንዲጠናከር እያደረገ ላለው ድጋፍ እና ክትትል በማመስገን፣ የልማት ማህበሩ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ፣ በቀጣይ ከንዑስ ልማት ማህበራት ጋር ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች እና የዳያስፖራ አባላት መጨመር ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በመጨረሻም የጂቡቲ ቅርንጫፍ ማህበር ከዋናው ጽ/ቤት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በቀጣይ የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት መክረዋል።


ማሳሰቢያ፤ (ሰኔ 12/2017ዓ.ም) ከላይ የተያያዘው የግለሰብ ፓስፖርት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ እንግዳ መቀበያ ክፍል ተጥሎ የተገኘ ሲሆን፣ አሁን ላይ በሚሲዮኑ የኢሚግሬሽን ክፍል ተቀምጦ ይገኛል። በመሆኑም የሚመለከተው ግለሰቡ ወይም ግለሰቡን የምታውቁት አካላት ይህንን መልዕክት እንድታስተላልፉ እንጠይቃለን። ከኤምባሲው፤


የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ በአይነት፣ በጥራት እና በብዛት እያደገ፣ በዓለም ገበያ ተፈላጊነትን እየጨመረ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ለግብርና እና ለሀገር በቀል ምርት ምቹ ስርዓትን በመፍጠር በኢኮኖሚ እድገት ላይ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።


ምክትል የሚሲዮኑ መሪ በጅቡቲ ከኦሮሚያ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት ተደረገ፤ (ሰኔ 04/2017 ዓ.ም) ምክትል የሚሲዮኑ መሪ ክቡር ከበደ አበራ በጅቡቲ ከኦሮሚያ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በማህበሩ አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም የልማት ማህበሩ በያዘው ዕቅድ መሠረት ከሌሎች ማህበራት ጋር በመቀናጀት በጅቡቲ የሚገኙ ዜጎቻችን የሀገሪቱን ሕግ አክብረው እንዲሰሩ እና በዚህም ማህበሩ አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርግ አሳስበዋል።


Les maquettes d’hydroélectricité et d’aéronautiquebrillent au Musée des Sciences d’Éthiopie! Le Premier ministre S.E. @AbiyAhmedAli a inauguré 5 expositions immersives. Ouvert au public — venez vous inspirer! 🇪🇹


ጣናነሽ 2 ጀልባ አዳማ ከተማ ደርሳለች። ጣናነሽ 2 ጀልባ አዳማ ስትደርስ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላታል። መጋቢት 30 ከጂቡቲ ዶላሬ ወደብ ተነስታ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞዋን የጀመረችው ጣናነሽ 2 ጀልባ፤ ባለፉት 2 ወራት እጅግ አስቸጋሪ በሆነ መልከዓ ምድር እያለፈች ጥንቃቄ የታከለበት ጉዞ እያደረገች ትገኛለች። ግንቦት 7 ቀን ወደ ኢትዮጵያ ከገባች ጀምሮ ላለፉት አንድ ወር ገደማ በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞችን እያቆራረጠች ነበር ጉዞዋን ስታደርግ የቆየችው። በዛሬው ዕለት ደግሞ አዳማ ከተማ ገብታለች። ይህች መርከብ በግዝፈቷም በአይነቷም ለየት ያለች ስትሆን፤ ለኢትዮጵያም ከጀልባነት በላይ ብዙ ተምሳሌታዊ ትርጉም አላት። 150 ሜትሪክ ቶን የምትመዝን ክብደት ሲኖራት ርዝመቷም 38 ሜትር ያህል ነው፤ 188 ሰው የመጫን አቅሟም አላት። የጀልባዋ ወደ ሀገር መግባት እና ሥራ መጀመር፤ በውሃ ትራንስፖርት፣ አጠቃላይ በውሃ ቱሪዝም እና በማሪታይም አገልግሎት ላይ የራሱን የሆነ ከፍ ያለ ድርሻ እና አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።


ሚሲዮኑ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር ተወያየ፤ (ሰኔ 2/2017 ዓ.ም) ሚሲዮኑ የትራንስፖርት ሚንስቴር ተወካይም እና የማሪታይም ባለስልጣን የጅቡቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ በተገኙበት ከኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር በስራ ቅንጅት፣ በስነ-ምግባር እና በአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት አድርጓል። ሚሲዮኑ ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ በሚደረገው የሀገራችን ገቢ-ወጪ ምርት የማጓጓዝ ሂደት ላይ ያሉ የአሠራር ክፍተቶችን በመለየት፣ የሎጂስቲክ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እና በውስጣዊ ቅንጅት ላይ በቅርበት ለመስራት እንዲቻል ውይይቱ ተገቢ መሆኑን ገልጿል። የአሽከርካሪዎች ማህበራት ተወካዮች በበኩላቸው በኮሪደሩ መሠረተ-ልማት የሚጋጥሙ እክሎች፣ የስራ መስተጓገል፣ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ እና ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቅሰዋል። የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተወካይም ከአሸከርካሪዎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች አገልግሎትን ለማሳለጥ አስፈላጊ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በተገቢው አሠራር መሠረት በፍጥነት መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል። በመጨረሻም ሚሲዮኑ በዘርፉ የሚስተዋሉ ቴክኒካል ችግሮችን በየጊዜው በመወያየት እና አገልግሎትን በተቀናጀ መልኩ በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አሳውቋል።
