Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 7, 2025 at 06:06 PM
*በጅቡቲ የትግራይ ልማት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ፤*
በጂቡቲ የትግራይ ልማት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በኮሚዩኒቲ አዳራሽ ተካሂዷል።
ጠቅላላ ጉባኤው ላይ የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር ከበደ አበራ፣ የማህበሩ አባላት፣ የክልሉ ደጋፊዎች፣ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።
በመድረኩም ምክትል የሚሲዮን መሪ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት ያስተላላፉ ሲሆን፣ ኤምባሲው እንደሁልጊዜው ለሌሎች አቻ ማህበራት አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ሁሉ ማህበሩን ለማጠናከር እና ለመደገፍ ከጎናችው እንደሚቆም ገልጿል።
በመጨረሻም የልማት ማህበሩን የሚመሩት ሰባት አባላት የያዘ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመምረጥ እና በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
🙏
1