Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
Ethiopian Embassy In Djibouti - የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ
February 11, 2025 at 01:17 PM
*የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፤* የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን የምስረታ መድረክ በቢሾፍቱ እየተካሄደ ይገኛል። የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያቀረቡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን መመስረት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የመሰረተ-ልማት ዝርጋታን በዘመናዊ መንገድ የቁጥጥር ስርዓት በመታገዝ የተሻለ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ሁለቱን አገራት የሚያገናኙ የትራንስፖርት መስመሮች ጋር በተያያዘ የሁለቱን አገራት የንግድ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እና በዘርፉ የሚስተዋለውን የህገ-ወጥ ንግዶችን በመቆጣጠር ህጋዊ የንግድ ስርዓትን እንዲስፋፋ በማድረግ ረገድ የጎላ አስተዋጾ እንዳለው አንስተዋል። የሁለቱን አገራት የትራንስፓርት ተቋማት በማቀናጀት በኮሪደሮች የሚኖረውን የንግድ ፍሰት ምቹ ከማድረግ አንጻር ለሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት፣ ኢኮኖሚያዊ እድገት ብሎም የቀጣናዊ ትስስሩን በማጠናከር ወደ ተሻለ የንግድ ምዕራፍ እንደሚወስድ ተገልጿል። በመድረኩ ላይ የጅቡቲ መሰረተ-ልማት እና ኢኪዩፕመንት ሚኒስትር ሚስተር ሀሰን ሀሙድ፣ የጅቡቲ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር ሚስተር መሀመድ ዋርሳማ እና ሌሎች የሁለቱ አገራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስብሰባው በሚቀጥሉት ቀናትም የሚቀጥል ይሆናል።

Comments